ኤርምያስ 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እንዲህም አለ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የይሁዳ ሕዝብ ወደሚሰግዱበት ወደ ቤተ መቅደሱ የቅጽር በር ላከኝ፤ በዚያ ቆሜ እንድነግራቸው ያዘዘኝ ቃል ይህ ነው፦ “የአኗኗራችሁንና የተግባራችሁን ሁኔታ ለውጡ፤ እኔም በዚህች ምድር እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። |
በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
“በእግዚአብሔር ቤት በር ቁም፤ ይህንም ቃል እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ለእግዚአብሔር ትሰግዱ ዘንድ በእነዚህ በሮች የምትገቡ ከይሁዳ ያላችሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።