ኤርምያስ 6:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ሁሉ እጅግ ደንቆሮዎች ናቸው፤ በጠማማነት ይሄዳሉ፤ ሁሉም እንደ ናስና ብረት የዛጉ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም ለማማት የሚዞሩ፣ ድድር ዐመፀኞች፣ ናስና ብረት የሆኑ፣ ምግባረ ብልሹዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ሁሉ እጅግ ዓመፀኞች ናቸው፤ በጠማማነት ይሄዳሉ፤ ናስና ብረት ናቸው፤ ሁሉ ርኩሰትን ያደርጋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም እንደ ነሐስና እንደ ብረት የጠነከሩ፤ በእልህም የተወጠሩ ዐመፀኞች ናቸው። ሁሉም የተበላሹ የሐሜት ሱሰኞች ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ሁሉ እጅግ ዓመፀኞች ናቸው፥ በጠማማነት ይሄዳሉ፥ ናስና ብረት ናቸው፥ ሁሉ ርኵሰትን ያደርጋሉ። |
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
በእኔ ላይ የተሰበሰቡና የከበቡኝን የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ፤ መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እንነሣለን” ይላሉ።
አንተም፦ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እውነት ጠፍቶአል፤ ከአፋቸውም ተቈርጦአል ትላቸዋለህ።
“ምላሳቸውን ለሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ በጠማማነት ይሄዳልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፤ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።
በርኵሰትሽ ሴሰኝነት አለ፤ አነጻሁሽ፤ አልነጻሽምና መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ እንግዲህ ከርኵሰትሽ አትነጺም።
አሕዛብም ተቈጡ፤ ቍጣህም መጣ፤ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፤ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”