እነሆ በምድሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይሁዳም ነገሥታት በአለቆችዋና በካህናቷ ላይ፥ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገች ከተማ፥ እንደ ብረትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ።
ኤርምያስ 6:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተፈታኝ ሕዝቤ መካከል ፈታኝ አድርጌሃለሁ፤ መንገዳቸውንም በፈተንሁ ጊዜ ታውቀኛለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ብረት እንደሚፈተን፣ የሕዝቤን መንገድ፣ አካሄዳቸውንም እንድትፈትን፣ አንተን ፈታኝ አድርጌሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መንገዳቸውን እንድታውቅና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል አቅላጭና ፈታኝ አድርጌሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤርምያስ ሆይ! ብረት እንደሚፈተን ሕዝቤን ፈትነህ ምን ዐይነት እንደ ሆኑ ዕወቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዳቸውን እንድታውቅና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል ፈታኝ አድርጌሃለሁ። |
እነሆ በምድሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይሁዳም ነገሥታት በአለቆችዋና በካህናቷ ላይ፥ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገች ከተማ፥ እንደ ብረትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ፤ እፈትናቸውማለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እንደዚሁ አደርጋለሁና።