Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 22:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ደም በም​ታ​ፈ​ስስ ከተማ ላይ ትፈ​ር​ዳ​ለ​ህን? ርኵ​ሰ​ቷን ሁሉ አስ​ታ​ው​ቃት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ አትፈርድባትምን? ደም በምታፈስሰው በዚህች ከተማ ላይ አትፈርድባትምን? ጸያፍ ተግባሯን ፊት ለፊት ንገራት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርዳለህን? ደም በምታፈስስ ከተማ ላይ ትፈርዳለህን? ርኩሰትዋን ሁሉ አስታውቃት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! በነፍሰ ገዳዮች የተሞላችውን ከተማ ልትፈርድባት ተዘጋጅተሃልን? እንግዲያውስ የፈጸመቻቸውን አጸያፊ ነገሮች ሁሉ ገልጠህ አሳያት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርዳለህን? ደም በምታፈስስ ከተማ ላይ ትፈርዳለህን? ርኵሰትዋን ሁሉ አስታውቃት።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 22:2
22 Referencias Cruzadas  

ደግ​ሞም ምናሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠራ ዘንድ ይሁ​ዳን ካሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሌላ ከዳር እስከ ዳር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ሞ​ላት ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደምን አፈ​ሰሰ።


በኀ​ይ​ልህ ጩኽ፤ አት​ቈ​ጥብ፤ ድም​ፅ​ህን እንደ መለ​ከት አንሣ፤ ለሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን፥ ለያ​ዕ​ቆብ ቤትም በደ​ላ​ቸ​ውን ንገር።


ልጆ​ቻ​ች​ሁን በከ​ንቱ ቀሥ​ፌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተግ​ሣ​ጼን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁም፤ ሰይ​ፋ​ችሁ እን​ደ​ሚ​ሰ​ብር አን​በሳ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በል​ቶ​አል፤ በዚ​ህም አል​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝም።


በእ​ጆ​ች​ሽም የን​ጹ​ሓን ድሆች ደም ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግ​ልጥ አገ​ኘ​ሁት እንጂ በጕ​ድ​ጓድ ፈልጌ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም።


በዚ​ህች ከተማ ውስጥ ግዳ​ዮ​ቻ​ች​ሁን አብ​ዝ​ታ​ች​ኋል፤ በጎ​ዳ​ና​ዎ​ች​ዋም ሙታ​ና​ች​ሁን ሞል​ታ​ች​ኋል።


ነገር ግን በቀ​ልን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሰው ልጅ ሆይ! የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት አስ​ታ​ው​ቃ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እን​ዲ​ህም በላት፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እን​ዲ​ደ​ርስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ደምን የም​ታ​ፈ​ስሺ፥ እን​ድ​ት​ረ​ክ​ሺም በራ​ስሽ ላይ ጣዖ​ታ​ትን የም​ታ​ደ​ርጊ ከተማ ሆይ!


“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዝገቷ ላለ​ባት፥ ዝገ​ቷም ከእ​ር​ስዋ ላል​ወጣ ድስት፥ ለደም ከተማ ወዮ​ላት! ቍራጭ ቍራ​ጩን አውጣ፤ ዕጣ አል​ወ​ደ​ቀ​ባ​ትም።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለደም ከተማ ወዮ​ላት! እኔ ደግሞ ማገ​ዶ​ዋን ታላቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የይ​ሁዳ ቤት ኀጢ​አት እጅግ በዝ​ቶ​አል፤ ምድ​ሪ​ቱም በብዙ አሕ​ዛብ እንደ ተመ​ላች ከተ​ማ​ዪ​ቱም እን​ዲሁ ዓመ​ፅ​ንና ርኵ​ሰ​ትን ተሞ​ል​ታ​ለች፤ እነ​ር​ሱም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን ትቶ​አ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አያ​ይም” ብለ​ዋል።


ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ።


ለደም ከተማ ወዮላት! በሁለንተናዋ ሐሰትና ቅሚያ ሞልቶባታል፣ ንጥቂያ ከእርስዋ አያልቅም።


ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችኋል።


ሕዝቡም ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን፤” አሉ።


ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ እስ​ከ​ዚ​ህች ትው​ልድ ድረስ ስለ ፈሰ​ሰው ስለ ነቢ​ያት ሁሉ ደም ይበ​ቀ​ላ​ቸው ዘንድ፥


አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከነ​ቢ​ያት ያላ​ሳ​ደ​ዱት ማን አለ? ዛሬም እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ የሰ​ጣ​ች​ሁ​ት​ንና የገ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን መም​ጣት አስ​ቀ​ድ​መው የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ገደ​ሉ​አ​ቸው።


ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኀጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos