La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 52:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢኮ​ን​ያን በተ​ማ​ረከ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት፥ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን፥ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ዮር​ማ​ሮ​ዴቅ በነ​ገሠ በአ​ን​ደ​ኛው ዓመት የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ኮ​ን​ያ​ንን ራስ ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ ከወ​ህ​ኒም አወ​ጣው፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ ዮርማሮዴክ በባቢሎን ነገሠ፤ በዚሁ ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ዐምስተኛው ቀን የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን ዐሰበው፤ ከእስር ቤትም አወጣው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዓሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ኤዌል ማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት ለይሁዳ ንጉሥ ለዮአኪን ቸርነት አደረገለት ከእስር ቤትም አወጣው፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ኤዌል መሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከእስር ፈታው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም ሆነ፥ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የዮአኪንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ ከወህኒም አወጣው፥

Ver Capítulo



ኤርምያስ 52:31
8 Referencias Cruzadas  

እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ፈር​ዖን ሹመ​ት​ህን ያስ​ባል፤ ወደ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃ​ነ​ት​ህም ይመ​ል​ስ​ሃል፤ ጠጅ አሳ​ላፊ በነ​በ​ር​ህ​በት ጊዜ ስታ​ደ​ር​ገው እንደ ነበ​ረው እንደ ቀድ​ሞው ሹመ​ት​ህም የፈ​ር​ዖ​ንን ጽዋ በእጁ ትሰ​ጣ​ለህ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈር​ዖን የተ​ወ​ለ​ደ​በት ዕለት ነበር፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱም ሁሉ ግብር አደ​ረገ፤ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹን አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹን አለቃ በአ​ሽ​ከ​ሮቹ መካ​ከል ዐሰበ።


ራስ​ህን ብታ​ዋ​ርድ ሰውም ኰራ​ብኝ ብትል፥ ራሱን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ውን ሰው ያድ​ነ​ዋል።


የል​መ​ና​ዬን ቃል ሰም​ቶ​ኛ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


አንተ ግን አቤቱ፥ መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤ ክብ​ሬና ራሴን ከፍ ከፍ የም​ታ​ደ​ር​ገው አንተ ነህ።


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሽ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ይመልሳታል፥ በዚያም ትቈያለች።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በይ​ሁዳ ያነ​ገ​ሠው የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ በኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ በኢ​ኮ​ን​ያን ፋንታ ነገሠ።