ኤርምያስ 52:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናቡከደነፆር የማረከው ሕዝብ ይህ ነው፤ በሰባተኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሃያ ሦስት አይሁድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡከደነፆር ማርኮ የወሰደው ሕዝብ ቍጥር እንደሚከተለው ነው፦ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት፣ ሦስት ሺሕ ሃያ ሦስት አይሁድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናቡከደነፆር ማርኮ ያፈለሰው የሕዝብ ቍጥር ብዛት ይህ ነው፤ በሰባተኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሀያ ሦስት አይሁድ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆር ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ብዛት ማስታወሻ ይህ ነው፤ በነገሠ በሰባተኛ ዓመቱ የማረካቸው ሦስት ሺህ ኻያ ሦስት አይሁድ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናቡከደነፆር የማረከው ሕዝብ ይህ ነው፥ በሰባተኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሀያ ሦስት አይሁድ፥ |
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
ሄ። ስለ ኀጢአቷ ብዛት እግዚአብሔር አዋርዶአታልና የሚዘባበቱባት በራስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላቶችዋም ተደሰቱ፤ ሕፃናቶችዋም በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።
ደግሞም፦ እኔ ምልክታችሁ ነኝ፤ እኔ እንዳደረግሁ እንዲሁ ይደረግባቸዋል፥ እነርሱንም ማርከው ይወስዷቸዋል በል።