La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 51:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ባቢ​ሎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ውስጥ ምድ​ርን ሁሉ ያሰ​ከ​ረች የወ​ርቅ ጽዋ ነበ​ረች፤ አሕ​ዛ​ብም ከጠ​ጅዋ ጠጥ​ተ​ዋል፤ ስለ​ዚህ አሕ​ዛብ ተን​ገ​ዳ​ግ​ደ​ዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ የወርቅ ጽዋ ነበረች፤ ምድርንም ሁሉ አሰከረች። ሕዝቦች ከወይን ጠጇ ጠጡ፤ ስለዚህ አሁን አብደዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ባቢሎን በጌታ እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፥ አሕዛብም ከወይን ጠጅዋ ጠጥተዋል፤ ስለዚህ አሕዛብ እንደ እብድ ሆነዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መላው ዓለም ከእርስዋ ጠጥቶ ይሰክር ዘንድ ባቢሎን በእኔ እጅ እንደ ወርቅ ዋንጫ ነበረች፤ አሕዛብ ሁሉ የእርስዋን ወይን ጠጅ ጠጥተው አእምሮአቸውን ሳቱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፥ አሕዛብም ከጠጅዋ ጠጥተዋል፥ ስለዚህ አሕዛብ አብደዋል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 51:7
16 Referencias Cruzadas  

ይህ​ንም ሙሾ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ታነ​ሣ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፥ “አስ​ጨ​ናቂ እን​ዴት ዐረፈ! አስ​ገ​ባ​ሪም እን​ዴት ጸጥ አለ!


አን​ተም እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚ​ህች ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ፥ በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ነገ​ሥ​ታት፥ ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ነቢ​ያ​ቱ​ንም፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ሁሉ በስ​ካር እሞ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እነሆ ልኬ የሰ​ሜ​ንን ወገ​ኖች ሁሉ፤ ባሪ​ያ​ዬ​ንም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ችም ምድ​ርና በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ሰዎች ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፈጽ​ሜም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጥ​ፋ​ትና ለፉ​ጨት ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ዕፍ​ረት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እር​ስዋ የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች ምድር ናትና፥ እነ​ር​ሱም በደ​ሴ​ቶ​ችዋ ይመ​ካ​ሉና ሰይፍ በው​ኆ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ር​ቃሉ።


የበ​ገ​ና​ውን አው​ታር ድምፅ ይቃ​ኛሉ፤ ከብዙ ሰዎ​ችም ጉባኤ ጋር ሰካ​ራ​ሞቹ ከም​ድረ በዳ መጡ፤ በእ​ጃ​ቸው አን​ባር፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም የተ​ዋበ አክ​ሊል አደ​ረጉ።


ሌላም ሁለተኛ መልአክ “አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው።


የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ፤” ብሎ ተናገረኝ።


ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፤ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤


የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”


አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሣ ወድቀዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኀይል የተነሣ ባለጠጋዎች ሆኑ፤” ብሎ ጮኸ።