“ለወገብህ የገዛሃትን ያቺን መታጠቂያ ወስደህ ተነሥ፤ ወደ ኤፍራጥስም ሂድ፤ በዚያም በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽጋት።”
ኤርምያስ 51:63 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም መጽሐፍ ማንበብ ከፈጸምህ በኋላ፥ ድንጋይን እሰርበት፤ በኤፍራጥስም ወንዝ ውስጥ ጣለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ብራና አንብበህ ከጨረስህ በኋላ፣ ድንጋይ አስረህበት ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ጣለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም መጽሐፍ ማንበብ ከፈጸምህ በኋላ፥ ድንጋይን እሰርበት በኤፍራጥስም ወንዝ መካከል ጣለው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠራያ ሆይ! ይህን መጽሐፍ ለሕዝቡ አንብበህ ከጨረስክ በኋላም መጽሐፉን ከድንጋይ ጋር አስረህ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወርውረህ ጣለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም መጽሐፍ ማንበብ ከፈጸምህ በኋላ፥ ድንጋይን እሰርበት በኤፍራጥስም ውስጥ ጣለው፥ |
“ለወገብህ የገዛሃትን ያቺን መታጠቂያ ወስደህ ተነሥ፤ ወደ ኤፍራጥስም ሂድ፤ በዚያም በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽጋት።”
የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፥ ለእነርሱ አምላካቸው እግዚአብሔር የላከውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ መናገርን በፈጸመ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤
አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።