ኤርምያስ 51:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሻገሪያዎችዋም ተይዘዋልና፥ ቅጥርዋም በእሳት ተቃጥሎአልና፥ ሰልፈኞችም ተማርከዋልና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካዎቿ እንደ ተያዙ፣ የወንዝ ዳር ምሽጎቿ እንደ ተቃጠሉ፣ ወታደሮቿም እንደ ተደናገጡ ሊነግሩት ይሯሯጣሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንዙም መሻገርያዎች ተይዘዋል፥ የውኃ ማቆርያዎቹም በእሳት ተቃጥለዋል ወታደሮቹም በሽብር ውስጥ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጠላት ሠራዊት የወንዙን መሸጋገሪያ ይዞ የዘብ መጠበቂያዎቹን አቃጠለ፤ የባቢሎን ወታደሮች በመሸበር ተርበደበዱ፤ |
እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃጠላሉ፤ ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኀይል አያድኑም፤ እንደ እሳትም ፍም ይሆኑብሻል፤ በላያቸውም ትቀመጫለሽ።
የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋትን ትተዋል፤ በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸውም ጠፍቶአል፤ እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ሯጩ ሯጩን ለመገናኘት፤ መልእክተኛውም መልእክተኛውን ለመገናኘት ይሮጣል፤ ከተማዋ ከዳር እስከ ዳር ተይዛለችና፤
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የባቢሎን ንጉሥ ቤት እንደ ተረገጠ አውድማ ናት፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።
ከተማዪቱም ተሰበረች፤ ሰልፈኞችም ሁሉ ሸሹ፤ በሁለቱም ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሥ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማዪቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓረባም መንገድ ሄዱ።