ኤርምያስ 51:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ምሎአል፦ በእውነት ሰዎችን እንደ አንበጣ እሞላብሻለሁ፤ እነርሱም እየሮጡ ይወርዱብሻል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ምሏል፤ እንደ አንበጣ መንጋ በሆነ ብዙ ሰው አጥለቀልቅሻለሁ፤ እነርሱም በድል አድራጊነት በላይሽ ያቅራራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ሲል በራሱ ምሎአል፦ በእውነት ብዛታቸው እንደ አንበጣ በሚሆኑ ሰዎች እሞላሻለሁ፥ እነርሱም የአሸናፊነትን ጩኸት የይጮኹብሻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ በባቢሎን ላይ ብዛቱ እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ሠራዊት እንደሚያመጣባት በስሙ ምሎአል፤ ያም ሠራዊት ድልን በመቀዳጀት ይደነፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ምሎአል፦ በእውነት ሰዎችን እንደ አንበጣ እሞላብሻለሁ፥ እነርሱም ጩኸት ያነሡብሻል። |
ስለዚህ እናንተ በግብፅ ምድር የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ በታላቁ ስሜ ምያለሁ፥” ይላል እግዚእብሔር።
ሊቈጠሩ የማይችሉ የዱርዋን ዛፎች ይቈርጣሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከአንበጣ ይልቅ በዝተዋልና፥ ቍጥርም የላቸውምና።
ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰደቢያና መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከተሞችዋም ሁሉ ለዘለዓለም ባድማ ይሆናሉ።
እጆችዋ ደክመዋልና ክበቡአት፤ ግንቧ ወድቋል፤ ቅጥርዋም ፈርሶአል፤ የእግዚአብሔርም በቀል ነውና ተበቀሏት፤ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
“በምድር ላይ ዓላማን አንሡ፤ በአሕዛብም መካከል መለከትን ንፉ፤ አሕዛብንም ለዩባት፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት እዘዙባት፤ ጦረኞችንም በላይዋ አቁሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ የሆኑ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ።
ጌታ እግዚአብሔር፥ “የያዕቆብን ትዕቢት አረክሳለሁ፤ ሀገሮቹንም ጠላሁ፤ ከተሞቹንም ከሚኖሩባቸው ሰዎች ጋር አጠፋለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአልና።
እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው በብዛት እንደ አንበጣ ሆነው ይመጡባቸው ነበር፤ ለእነርሱና ለግመሎቻቸው ቍጥር አልነበራቸውም፤ ምድሪቱንም ያጠፏት ዘንድ ይመጡ ነበር።