ኤርምያስ 50:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፤ በተራሮችም ላይ የተቅበዘበዙ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ ዐለፉ፤ በረታቸውንም ረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቷቸው፤ በተራሮችም ላይ እንዲቅበዘበዙ አደረጓቸው፤ በተራራና በኰረብታ ላይ ተንከራተቱ፤ ማደሪያቸውንም ረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፥ ከተራሮችም ላይ እንዲያፈገፍጉ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ ሄደዋል፥ በረታቸውንም ረስተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሕዝቤ እንደ ጠፉ በጎች ሆነዋል፤ ጠባቂዎቻቸውም አሳቱአቸው፤ በተራራ ላይ ባዝነው እንዲቀሩም አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኰረብታ እንደሚባዝኑ በጎች ተንከራተቱ፤ ማደሪያቸውንም ረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፥ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፥ በተራሮችም ላይ የተቅበዘበዙ አደረጉአቸው፥ ከተራራ ወደ ኮረብታ አለፉ፥ በረታቸውንም ረሱ። |
የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “ብትጸጸትና ብታለቅስ ትድናለህ፤ የት እንዳለህም ታውቃለህ፤ በከንቱ ታምነሃልና፤ ኀይላችሁም ከንቱ ይሆናል፤ እናንተ ግን መስማትን እንቢ አላችሁ፤
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም ስለ ኀጢአታችን ለሞት አሳልፎ ሰጠው።
እረኞች አእምሮአቸውን አጥተዋልና፥ እግዚአብሔርንም አልፈለጉትምና፤ ስለዚህም መሰማሪያውን አላወቁም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
ሳይጨልምባችሁ፥ ጨለማም ባለባቸው ተራሮች እግሮቻችሁ ሳይሰነካከሉ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፤ በዚያም የሞት ጥላ አለና በጨለማውም ውስጥ ያኖራችኋልና ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ።
ከጥንት ጀምሬ ቀንበርሽን ሰብሬአለሁ፤ እስራትሽንም ቈርጫለሁ፤ አንቺም፦ አላገለግልም አልሽ፤ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፤ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
በእውነት የተራሮች ኀይል፥ የኮረብቶችም ኀይል ሐሰት ነው፤ ነገር ግን የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፥ “ከዳተኛዪቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ፥ ወደ ለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፤ በዚያም አመነዘረች።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት የእረኞች መኖሪያ ይሆናል።
“እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።”
እስራኤልንም ወደ ማሰማርያው እመልሳለሁ፥ በቀርሜሎስና በባሳን፥ በኤፍሬም ተራራና በገለዓድም ይሰማራል፤ ነፍሱም ትጠግባለች።
ሰላም ሳይኖር፦ ሰላም እያሉ ሕዝቤን አታልለዋልና፤ አንዱም ሰው ቅጥር ሲሠራ እነርሱ ያለገለባ ይመርጉታል፤ ይወድቃልም፤
በመልካም ማሰማርያ አስማራቸዋለሁ፤ ጕረኖአቸውም በረዥሞቹ በእስራኤል ተራሮች ላይ ይሆናል፤ በዚያ በመልካም ጕረኖ ውስጥ ይመሰጋሉ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ ማሰማርያ ይሰማራሉ።
እኔ ራሴ በጎችን አሰማራለሁ፤ አስመስጋቸውማለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የጠፋውንም እፈልጋለሁ፤ የባዘነውንም እመልሳለሁ፤ የተሰበረውንም እጠግናለሁ፤ የደከመውንም አጸናለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውንም እጠብቃለሁ፤ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ።”