እግዚአብሔርም፥ “የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳና አራዊት፥ እስከ ተንቀሳቃሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ።
ኤርምያስ 50:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤ ከሰሜን በእርስዋ ላይ ወጥትዋል፤ ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፤ የሚቀመጥባትም አይገኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰሜን አንድ መንግሥት መጥቶ ይወጋታል፤ ምድሯንም ባድማ ያደርጋል፤ የሚኖርባትም አይገኝም፤ ሰዎችና እንስሳትም ሸሽተው ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝብ ከሰሜን በእርሷ ላይ ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፥ የሚቀመጥባትም አይገኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባቢሎን ላይ አደጋ ጥሎ ምድረ በዳ የሚያደርጋት ሕዝብ ከሰሜን በኩል ተነሥቶባታል፤ ሰውም እንስሳውም ጥሎአት ይሸሻል፤ የሚኖርባትም የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝብ ከሰሜን ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፥ የሚቀመጥባትም አይገኝም፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል። |
እግዚአብሔርም፥ “የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳና አራዊት፥ እስከ ተንቀሳቃሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ።
እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ ሀገር አልፋለሁ፤ በግብፅም ሀገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ በቀልን አደርግባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ከሰሜንና ከፀሐይ መውጫ የሚመጡትን አስነሣሁ፤ በስሜም ይጠራሉ፤ አለቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እንደሚረግጥ ሸክላ ሠሪ እንዲሁ ይረግጡአቸዋል።
እግዚአብሔር አምላክ ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦
እነሆ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አነሣለሁ፤ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ፤ በእርስዋም ላይ ይሰለፋሉ፤ ከዚያም ትወሰዳለች፤ ፍላጾቻቸውም ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ብልህ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና ሰማይና ምድር፥ በእነርሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢሎን ደስ ይላቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።
አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ታጠፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተናግረሃል በል።
እንግዲህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።”
በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ።
ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው እንዳይቀመጥባቸው አጠፋቸዋለሁ።
ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፣ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፣ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።