የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
ኤርምያስ 50:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልንም ወደ ማሰማርያው እመልሳለሁ፥ በቀርሜሎስና በባሳን፥ በኤፍሬም ተራራና በገለዓድም ይሰማራል፤ ነፍሱም ትጠግባለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልንም ወደ መሰማሪያው እመልሰዋለሁ፤ በቀርሜሎስና በባሳን ላይ ይሰማራል፤ በኤፍሬም ተራሮችና በገለዓድም ላይ፣ እስኪጠግብ ይመገባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልንም ወደ ማሰማርያው እመልሳለሁ፥ በቀርሜሎስና በባሳንም ላይ ይሰማራል፥ ሆዱም በኤፍሬም ተራራና በገለዓድ ላይ ትጠግባለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ምድራቸው እመልሳለሁ፤ በቀርሜሎስ ተራራና በባሳን አውራጃ የሚበቅለውን ሁሉ ይመገባሉ፤ በኤፍሬምና በገለዓድ ከሚበቅለውም እህል የፈለጉትን ያኽል ይመገባሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልንም ወደ ማሰማርያው እመልሳለሁ፥ በቀርሜሎስና በባሳንም ላይ ይሰማራል፥ ሰውነቱም በኤፍሬም ተራራና በገለዓድ ላይ ትጠግባለች። |
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
የዮርዳኖስም ምድረ በዳ ያብባል፤ ሐሤትንም ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብርና የቀርሜሎስ ክብር ይሰጠዋል፤ ሕዝቤም የጌታን ክብር፥ የአምላክንም ግርማ ያያሉ።
የሕዝቤን ቅሬታ ከበተንኋቸው ምድር ሁሉ ወደ መሰማሪያቸው ሰብስቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይበዛሉ፤ ይባዛሉም።
በዚያም ዘመን የይሁዳ ቤት ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳል፤ በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
“እነሆ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከምርኮ ሀገር አድናለሁና ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ ያዕቆብም ይመለሳል፤ ያርፍማል፤ ተዘልሎም ይቀመጣል፤ ማንም አያስፈራውም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማዪቱም በጕብታዋ ላይ ትሠራለች፤ አዳራሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖሪያ ይሆናል።
የካህናቱንም የሌዊን ልጆች ሰውነት ከፍ ከፍ አደርጋታለሁ፤ አረካታለሁ፤ ሕዝቤም ከበረከቴ ይጠግባል፥” ይላል እግዚአብሔር።
በኤፍሬም ተራሮች ላይ የሚከራከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጠሩባት ቀን ትመጣለችና።”
እነሆ በቍጣዬና በመዓቴ፥ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት ሀገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤
“ነገር ግን አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ እነሆ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከተማረኩባት ምድር አድናለሁ፤ ያዕቆብም ተመልሶ ያርፋል፤ ተዘልሎም ይተኛል፤ ማንም አያስፈራውም።
“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፤ በተራሮችም ላይ የተቅበዘበዙ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ ዐለፉ፤ በረታቸውንም ረሱ።
ስለዚህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከአሕዛብ ዘንድ እቀበላቸዋለሁ፤ ከበተንሁባቸውም ሀገሮች እሰበስባቸዋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እሰጣቸዋለሁ።
ከአሕዛብም መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየሀገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም እመልሳችኋለሁ።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከኀጢአታችሁ ሁሉ በአነጻኋችሁ ጊዜ በከተሞች ሰዎችን አኖራለሁ፤ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ።
ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘለዓለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርስዋም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች፤ ሁሉም በሰላም ይቀመጡበታል።
የምሥራቁም ድንበር በሐውራን በደማስቆና በገለዓድ በእስራኤልም ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል። ከሰሜኑ ድንበር ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ባሕር እስከ ታማር ድረስ የምሥራቁ ድንበር ይህ ነው።
በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።
ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር የከብት ሀገር እንደ ነበረ አዩ።
እግዚአብሔር በእስራኤል ልጆች ፊት የሰጣት ምድር የከብት መሰማሪያ ሀገር ናት፤ ለእኛም ለአገልጋዮችህ ብዙ እንስሳት አሉን።
ኢያሱም፥ “ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ተራራማው የኤፍሬም ሀገርም ከጠበባችሁ ወደ ዱር ወጥታችሁ መንጥራችሁ አቅኑአት” አላቸው።