የተረፉትም ሁሉ እንደ ተባረረ ሚዳቋ፥ እንደ ባዘነ በግም ይሆናሉ። የሚሰበስባቸውም የለም፤ እንዲሁም ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ ይሸሻል።
ኤርምያስ 50:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ ከአረማዊው ሰይፍ ፊት የተነሣ እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ እያንዳንዱም ወደ ሀገሩ ይሸሻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባቢሎን ዘር የሚዘራውን፣ በመከር ጊዜ ማጭድ የጨበጠውንም ዐጫጅ አጥፉት፤ ከአጥፊው ሰይፍ የተነሣ፣ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለስ፤ ወደ ገዛ ምድሩም ይሽሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘሪውንና መከር ሰብሳቢውን ከባቢሎን አስወግዱ፤ በዚያች አገር የሚኖር እያንዳንዱ የውጪ ዜጋ አደጋ የሚጥልባትን ሠራዊት በመፍራት ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ወደ አገሩም ይሸሻል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፥ ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። |
የተረፉትም ሁሉ እንደ ተባረረ ሚዳቋ፥ እንደ ባዘነ በግም ይሆናሉ። የሚሰበስባቸውም የለም፤ እንዲሁም ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ ይሸሻል።
እንደ አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፤ ከአረማውያን ሰልፍና ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ ምድራቸው ምድረ በዳ ሆናለችና።”
ብዛታቸውም ደከመ፤ ወደቀም፤ አንዱም አንዱ ለጓደኛው፦ ተነሥ፤ ከአረማውያን ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባት ምድር እንመለስ አለው።
በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እበትናለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማዱን እበትናለሁ፤ በአንቺም አለቆችንና መሳፍንትን እበትናለሁ።
ባቢሎንን ፈወስናት፥ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ከዋክብትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ እንተዋት፤ ሁላችንም ወደ ሀገራችን እንሂድ።
መከሩ ከእርሻቸው ጠፍቶአልና ገበሬዎች ስለ ስንዴውና ስለ ገብሱ ዐፈሩ፤ የወይን አትክልተኞችም ስለ ወይኑ አለቀሱ።
ስለዚህ ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፤ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባላል፤ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ።