ኤርምያስ 49:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፤ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ወጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት የተነገረ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተነሡ፣ ቄዳርን ውጉ፤ የምሥራቅንም ሕዝብ ደምስሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ድል ስላደረጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፥ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ድል ስላደረጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተነሡ፤ በቄዳር ሕዝብ ላይ ዝመቱ፤ የምሥራቅንም ሕዝብ አጥፉ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታ ስለ ቄዳርና ስለ አሶር መንግሥታት፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፥ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ። |
አብርሃምም ለቁባቶቹ ልጆች ሀብትን ሰጣቸው፤ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ምሥራቅ ሀገር ሰደዳቸው።
ከብቶቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አምስት መቶም እንስት አህዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት፤ ሥራውም በምድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።
በባሕርም በኩል በፍልስጥኤማውያን መርከቦች ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፤ የምሥራቅ ሰዎችንና ኤዶምያስን በአንድነት ይዘርፋሉ፤ በሞዓብ ላይ ቀድመው እጃቸውን ይዘረጋሉ፤ የአሞንም ልጆች ቀድመው ለእነርሱ ይታዘዛሉ።
ምድረ በዳውና ከተሞችዋ፥ የቄዳርም ነዋሪዎችና መንደሮች ድምፃቸውን ያንሡ፤ በዋሻም የሚኖሩ እልል ይበሉ፤ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።
“ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማትን ሰምቻለሁ፤ በአሕዛብ ሀገሮች ተሰብሰቡ፤ በእርስዋም ላይ ኑ፤ እርስዋንም ውጓት፥ የሚል መልእክተኛ ተልኳል።
ዓረብና የቄዳር አለቆች ሁሉ የእጅሽ ነጋዴዎች ነበሩ፤ በግመሎችና በአውራ በጎች፥ በፍየሎችም በእነዚህ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር።
የእስራኤልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያንና አማሌቃውያን ይዘምቱባቸው ነበር፥ በምሥራቅም የሚኖሩ ልጆች አብረው ይዘምቱባቸው ነበር፤