ኤርምያስ 49:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዶምና ገሞራ፥ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ከተሞች እንደ ተገለበጡ፥ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር፤ እንዲሁ በዚያ ሰው አይቀመጥም፤ የሰው ልጅም አይኖርባትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዙሪያቸው ካሉት ከተሞች ጋራ፣ ሰዶምና ገሞራ እንደ ተገለበጡ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዶምና ገሞራ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ጎረቤቶቻቸው እንደ ተገለባበጡ፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ከሚገኙ ከተሞች ጋር በተደመሰሱ ጊዜ የደረሰባቸው ጥፋት እንዲሁ በተመሳሳይ በኤዶምም ላይ ይደርሳል። ዳግመኛም በዚያ ሰፍሮ የሚኖር ከቶ አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዶምና ገሞራ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ከተሞች እንደ ተገለበጡ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ በዚያ ሰው አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም። |
በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
ሰዶምንና ገሞራን፥ በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተሞች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም፤ የሰውም ልጅ አይኖርባትም።
ሰዶምንና ገሞራን አስቀድሜ እንደ ገለበጥኋቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፤ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ በዚህም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፣ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።
ኢሳይያስም አስቀድሞ እንደ ተናገረ “እግዚአብሔር ጸባኦት ዘር ያስቀረልን ባይሆን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን፥ ገሞራንም በመሰልን ነበር።”
“ከዚያም በኋላ የሚነሣ ትውልድ፥ ከእናንተም በኋላ የሚሆኑ ልጆቻችሁ ከሩቅ ሀገርም የሚመጣ እንግዳ፥ የዚችን ሀገር መቅሠፍት፥ እግዚአብሔርም በላይዋ የላከውን ሥቃይዋን፥
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳይዘራባትም፥ እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቍጣውና በመዓቱ እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥
እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።