La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 49:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ ጽዋ​ውን ያል​ተ​ገ​ባ​ቸው ሰዎች ጠጥ​ተ​ው​ታል፤ አን​ተም መን​ጻ​ትን ትነ​ጻ​ለ​ህን? እን​ግ​ዲህ አት​ነ​ጻም መጠ​ጣ​ትን ትጠ​ጣ​ለ​ህና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከጽዋው መጠጣት የማይገባቸው ሊጠጡ ግድ ከሆነ፣ አንተ እንዴት ሳትቀጣ ትቀራለህ? መቀጣትህ አይቀርም፤ መጠጣት ይገባሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፥ ጽዋውን መጠጣት የማይገባቸው ሰዎች ጠጥተውታል፤ አንተስ ሳትቀጣ ፈጽሞ ትቀራለህን? በእርግጥ ትጠጣለህ እንጂ ያለ ቅጣት አትቀርም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እንግዲህ መቀጣት የማይገባቸው ሰዎች እንኳ የቅጣቱን ጽዋ ገፈት የሚቀምሱ ከሆነ እናንተ ያለ ቅጣት የምታመልጡ ይመስላችኋልን? አይደለም፤ እናንተም ከቅጣቱ ጽዋ መጠጣት አለባችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ጽዋውን ያልተገባቸው ሰዎች ጠጥተውታል፥ አንተም ሳትቀጣ ትቀራለህን? በእርግጥ ትጠጣለህ እንጂ ያለ ቅጣት አትቀርም።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 49:12
9 Referencias Cruzadas  

በድሃ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ያነሣሣዋል፥ በሚጠፋም ላይ ደስ የሚለው ከፍርድ አይነጻም፥ የሚራራ ግን ምሕረትን ያገኛል።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፥ “ያል​ተ​በ​ረዘ የዚ​ህን ቍጣ የወ​ይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ አን​ተን የም​ሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ አጠ​ጣ​ቸው።


አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም የበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥” ያለ ቅጣ​ትም ከቶ አል​ተ​ው​ህም።”


“ነገር ግን አንተ ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! አት​ፍራ፥ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ! አት​ደ​ን​ግጥ፤ እነሆ አን​ተን ከሩቅ፥ ዘር​ህ​ንም ከተ​ማ​ረ​ኩ​ባት ምድር አድ​ና​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብም ተመ​ልሶ ያር​ፋል፤ ተዘ​ል​ሎም ይተ​ኛል፤ ማንም አያ​ስ​ፈ​ራ​ውም።


በቅ​ዱሱ ተራ​ራዬ ላይ እንደ ጠጣህ እን​ዲሁ አሕ​ዛብ ሁሉ ወይ​ንን ይጠ​ጣሉ፤ አዎን፥ ይጠ​ጣሉ፥ ይጨ​ል​ጡ​ማል፤ እን​ዳ​ል​ነ​በ​ሩም ይሆ​ናሉ።


ኢየሱስ ግን መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አለ። “እንችላለን” አሉት።