La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 48:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከሰ​ልፍ የሸሹ ከሐ​ሴ​ቦን ጥላ በታች ቆመ​ዋል፤ እሳት ከሐ​ሴ​ቦን፥ ነበ​ል​ባ​ልም ከሴ​ዎን ወጥ​ቶ​አል፤ የሞ​አ​ብ​ንም ማዕ​ዘን፥ የሚ​ጮኹ ልጆ​ች​ንም ራስ በል​ቶ​አል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“የሞዓብን ግንባር፣ የደንፊዎችን ዐናት የሚያቃጥል፣ እሳት ከሐሴቦን፣ ነበልባል ከሴዎን ቤት ወጥቷልና፤ ኰብላዮች በሐሴቦን ጥላ ሥር፣ ተስፋ ቈርጠው ቆመዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“የሸሹ ደክመው ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፤ እሳት ከሐሴቦን ነበልባልም ከሴዎን መካከል ወጥቶአል የሞዓብን ግንባር የሁከትንም ልጆች ዘውድ በልቶአል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሽሽት የደከሙ ስደተኞች በሐሴቦን ጥላ ሥር ተጠልለዋል፤ ይህም የሆነው እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሲሆን ቤቶች ወጥቶ የሞአብን ግንባር ቀደም ሠራዊትና ደጋፊ መሪዎችዋን አቃጥሎአል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሸሹ ደክመው ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፥ እሳት ከሐሴቦን ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአል የሞዓብንም ማዕዘን የሤትንም ልጆች አናት በልቶአል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 48:45
12 Referencias Cruzadas  

እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያወጣ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


የሜ​ም​ፎ​ስና የጣ​ፍ​ናስ ልጆች አስ​ነ​ወ​ሩሽ፤ አላ​ገ​ጡ​ብ​ሽም።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሞ​አብ ፈውስ የለም፤ በሐ​ሴ​ቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እን​ዳ​ት​ሆን እና​ጥ​ፋት” ብለው ክፉ ነገ​ርን አስ​በ​ው​ባ​ታል። ፈጽሞ ትተ​ዋ​ለች፤ ከኋ​ላዋ ሰይፍ ይመ​ጣ​ልና።


በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የከ​ተ​ሞ​ች​ዋ​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች፤ ሞዓ​ብም በድ​ካ​ምና በው​ካታ፥ በመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ይሞ​ታል፤


ከእርሱ ዘንድ የማዕዘኑ ድንጋይ፥ ከእርሱም ዘንድ ችንካሩ፥ ከእርሱም ዘንድ የሰልፍ ቀስት፥ ከእርሱም ዘንድ አስገባሪው ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ ወደ ሴዎን በሰ​ላም ቃል እን​ዲህ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤


ሐሴ​ቦ​ንም የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን ከተማ ነበረ፤ እር​ሱም የፊ​ተ​ኛ​ውን የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ወግቶ ከአ​ሮ​ኤር እስከ አር​ኖን ድረስ ምድ​ሩን ሁሉ ወስዶ ነበር።


እሳት ከሐ​ሴ​ቦን፥ ነበ​ል​ባ​ልም ከሴ​ዎን ከተማ ወጣ፤ እስከ ሞዓብ ድረስ በላ፤ የአ​ር​ኖን ሐው​ል​ቶ​ች​ንም ዋጠ፤


ሞዓብ ሆይ፥ ወዮ​ልህ! የካ​ሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለማ​ደን፥ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለም​ርኮ፤ ለአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ ለሴ​ዎን ሰጠ።


አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤ ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤ የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።


ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?