ኤርምያስ 48:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቂርዮት፥ በቦሶራ፥ በሞአብም ምድር ከተሞች ሁሉ ቅርብና ሩቅ በሆኑ ላይ ፍርድ መጥቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቂርዮትና በባሶራ ላይ፤ በሩቅና በቅርብ ባሉት በሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቂርዮት፥ በባሶራ፥ በሞዓብም ምድር በቅርብና በሩቅ ባሉ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤትምዖን ላይ፥ በቂርዮት፥ በባሶራ፥ በሞዓብም ምድር ከተሞች ሁሉ ቅርብና ሩቅ በሆኑ ላይ ፍርድ መጥቶአል። |
ከኤዶምያስ፥ ከባሶራ የሚመጣ፥ ልብሱም የቀላ፥ የሚመካ ኀይለኛ፥ አለባበሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የምከራከር፥ ስለ ማዳንም የምፈርድ እኔ ነኝ።
ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰደቢያና መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከተሞችዋም ሁሉ ለዘለዓለም ባድማ ይሆናሉ።
በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ የከተሞችዋንም መሠረቶች ትበላለች፤ ሞዓብም በድካምና በውካታ፥ በመለከትም ድምፅ ይሞታል፤
ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ባሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።
በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ በኩል ከሮቤል ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ በሚሶን ምድረ በዳ ቦሶርንና መሰማርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማርያዋን፤