ኤርምያስ 46:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፈረሶች ተቀመጡ፤ ሰረገሎችንም አዘጋጁና ውጡ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የሊብያ ኀያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኀያላን ይውጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈረሶች ሆይ ዘልላችሁ ውጡ፤ ሠረገሎችም ሸምጥጡ፤ ጋሻ ያነገባችሁ የኢትዮጵያና የፉጥ ሰዎች፣ ቀስት የገተራችሁ የሉድ ጀግኖች፣ እናንተ ብርቱ ጦረኞች ተነሥታችሁ ዝመቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈረሶች ሆይ! ውጡ፤ ሰረገሎችም ሆይ! ንጐዱ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፉጥ ኃያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈረሶች ወደ ፊት እንዲሄዱ፥ ሠረገሎችም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት እንዲሽከረከሩ እዘዙ፤ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ ጋሻቸውን አንግበው በመጡ ሰዎችና፥ ከልድያ በመጡ ቀስት በሚወረውሩ ኀያላን ሰዎች ጭምር የተጠናከሩ ወታደሮችን ላኩ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈረሶች ሆይ፥ ውጡ፥ ሰረገሎችም ሆይ፥ ንጐዱ፥ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፉጥ ኃያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ። |
በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ከሞት የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ኤላድ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬን ይናገራሉ።
ከኀይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መሽከርከር፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ወደ ልጆቻቸው አይመለሱም።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
ፋርስና ሉድ፥ ሊብያም በሠራዊትሽ ውስጥ ሰልፈኞችሽ ነበሩ፤ ጋሻና ራስ ቍርም በአንቺ ውስጥ ያንጠለጥሉ ነበር፤ እነርሱም ክብርሽን ሰጡ።
ሰይፍ በግብፅ ላይ ይመጣል፤ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፤ የተገደሉትም በግብፅ ውስጥ ይወድቃሉ፤ ብዛቷንም ይወስዳሉ፤ መሠረቷም ይፈርሳል።
ኢትዮጵያና ፉጥ፥ ሉድም፥ ዓረብም ሁሉ፥ ኩብም፤ ሊብያም፤ ቀርጤስም የተደባለቀ ሕዝብም ሁሉ፥ ቃል ኪዳንንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።