“ጋሻና ጦር ያዙ፤ ወደ ሰልፍም ቅረቡ።
“ትልቁንና ትንሹን ጋሻ አዘጋጁ፤ ለውጊያም ውጡ!
ጋሻንና አላባሽን አዘጋጁ ወደ ጦርነትም ቅረቡ።
“ጋሻችሁን አዘጋጁ፤ ወደ ጦር ሜዳም ዝመቱ፤
ጋሻ ጦር አዘጋጁ ወደ ሰልፍም ቅረቡ።
ማዕዱን አዘጋጁ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እናንተ አለቆች ሆይ፥ ተነሡ፤ ጋሻውንም አዘጋጁ።
“በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶልም አውሩ፤ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ።
“ይህን በአሕዛብ መካከል ዐውጁ፤ ለሰልፍ ተዘጋጁ፤ ኀያላንን አስነሡ፤ ሰልፈኞች ሁሉ ይቅረቡ፤ ይውጡም።
የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቶአል፣ ምሽግን ጠብቅ፥ መንገድንም ሰልል፣ ወገብህን አጽና፥ ኃይልህንም እጅግ አበርታ።
ከብበው ያስጨንቁሻልና ውኃን ቅጂ፣ አምባሽን አጠንክሪ፣ ወደ ጭቃ ገብተሽ እርገጪ፣ የጡብን መሠሪያ ያዢ።