Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 46:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ፈረ​ሰ​ኞች ሆይ፥ ፈረ​ሶ​ችን ጫኑና ውጡ፤ ራስ ቍር​ንም ደፍ​ታ​ችሁ ቁሙ፤ ጦር​ንም ሰን​ግሉ፤ ጥሩ​ር​ንም ልበሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ፈረሶችን ጫኑ፤ በላያቸውም ተቀመጡ! የራስ ቍር ደፍታችሁ፣ በየቦታችሁ ቁሙ፤ ጦራችሁን ወልውሉ፤ ጥሩራችሁን ልበሱ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ፈረሰኞች ሆይ! ፈረሶችን ለጉሙና ውጡ፥ ራስ ቁርንም ደፍታችሁ በቦታችሁ ቁሙ፤ ጦርንም ሰንግሉ ጥሩርንም ልበሱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ፈረሶቻችሁን ለጒማችሁ ርካብ ረግጣችሁ ውጡ፤ የራስ ቊር ደፍታችሁ ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ጦራችሁን ወልውሉ፤ የጦር ልብሳችሁንም ልበሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ፈረሰኞች ሆይ፥ ፈረሶችን ለጕሙና ውጡ፥ ራስ ቍርንም ደፍታችሁ ቁሙ፥ ጦርንም ሰንግሉ ጥሩርንም ልበሱ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 46:4
11 Referencias Cruzadas  

ዖዝ​ያ​ንም ለጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋሻና ጦር፥ ራስ ቍርና ጥሩር፥ ቀስ​ትና የሚ​ወ​ነ​ጭ​ፉ​ትን ድን​ጋይ አዘ​ጋ​ጀ​ላ​ቸው።


ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እኩ​ሌ​ቶቹ ብላ​ቴ​ኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስ​ትና ጥሩ​ርም ይዘው በፊ​ትና በኋላ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ከይ​ሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።


አሕ​ዛብ ሆይ፥ ዕወ​ቁና ደን​ግጡ፤ እስከ ምድር ዳር​ቻም ስሙ፤ ኀያ​ላን! ድል ሁኑ፤ ዳግ​መ​ኛም ብት​በ​ረቱ እንደ ገና ድል ትሆ​ና​ላ​ችሁ።


“በግ​ብፅ ተና​ገሩ፤ በሚ​ግ​ዶ​ልም አውሩ፤ በሜ​ም​ፎ​ስና በጣ​ፍ​ናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙ​ሪ​ያህ ያለ​ውን በል​ቶ​አ​ልና፦ ተነሥ ተዘ​ጋ​ጅም በሉ።


“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል ነውና።


በቀ​ስት ወር​ዋ​ሪው ላይ፥ በጥ​ሩ​ርም በሚ​ነ​ሣው ላይ ቀስ​ተ​ኛው ቀስ​ቱን ይገ​ትር፤ ለጐ​በ​ዛ​ዝቷ አት​ዘኑ፤ ሠራ​ዊ​ቷ​ንም ሁሉ አጥፉ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሞን ልጆ​ችና ስለ ስድ​ባ​ቸው እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመ​ግ​ደል ተመ​ዝ​ዞ​አል፤ ጨር​ሶም ያርድ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሎ​አል በል።


“ይህን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ዐውጁ፤ ለሰ​ልፍ ተዘ​ጋጁ፤ ኀያ​ላ​ንን አስ​ነሡ፤ ሰል​ፈ​ኞች ሁሉ ይቅ​ረቡ፤ ይው​ጡም።


ሳኦ​ልም ለዳ​ዊት ጥሩር አለ​በ​ሰው፤ በራ​ሱም ላይ የናስ ቍር ደፋ​ለት።


በራ​ሱም የናስ ቍር ደፍቶ ነበር፤ ጥሩ​ርም ለብሶ ነበር፤ የጥ​ሩ​ሩም ሚዛን አም​ስት ሺህ ሰቅል ናስና ብረት ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos