በተራራው ላይ፥ ያም ባይሆን በአንድ ቦታ ተሰውሮአልና ከእነርሱ ፊተኞቹ ቢወድቁ የሚሰማው ሁሉ አቤሴሎምን የተከተለ ሕዝብ ተመታ ይላል።
ኤርምያስ 41:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን ሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጕድጓድ ነበረ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስማኤል ከጎዶልያስ በተጨማሪ የገደላቸው ሰዎች ሁሉ ሬሳ የተጣለበት የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ፣ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ ለመከላከል ያሠራው ነበር፤ ይህን ጕድጓድ የናታንያ ልጅ እስማኤል በሬሳ ሞላው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጉድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ለመመከት የሠራው ምሽግ ነበረ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያን ሰዎች ገድሎ የጣለበትም ያ ጒድጓድ የእስራኤል ንጉሥ ባዕሻ አደጋ በጣለበት ጊዜ ንጉሥ አሳ ለመጠባበቂያ አስቈፍሮት የነበረ ትልቅ ጒድጓድ ነበር፤ እስማኤል ያን ጒድጓድ በሬሳ ሞላው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጕድጓድ ነበረ፥ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት። |
በተራራው ላይ፥ ያም ባይሆን በአንድ ቦታ ተሰውሮአልና ከእነርሱ ፊተኞቹ ቢወድቁ የሚሰማው ሁሉ አቤሴሎምን የተከተለ ሕዝብ ተመታ ይላል።
የምድያምም እጅ በእስራኤል ላይ ጠነከረች፤ ከምድያምም ፊት የተነሣ የእስራኤል ልጆች በተራሮችና በገደሎች ላይ ጕድጓድና ዋሻ፥ ምሽግም አበጁ።
የእስራኤልም ሰዎች ወደ እነርሱ መሄድ እንደሚያስጨንቃቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋሻና በግንብ፥ በገደልና በቋጥኝ፥ በጕድጓድም ውስጥ ተሸሸጉ።
ሁለታቸውም ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር ገቡ፤ ፍልስጥኤማውያንም “እነሆ፥ ዕብራውያን ከተሸሸጉበት ጕድጓድ ይወጣሉ” አሉ።
በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር የተሸሸጉት እስራኤል ሁሉ ፍልስጥኤማውያን እንደ ሸሹ በሰሙ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ሊዋጉአቸው ተከተሉአቸው።
ሳኦልም ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊትንና ሰዎቹንም ለመፈለግ ዋሊያዎች ወደሚታደኑባቸው ዓለቶች ሄደ።