አክዓብም ኤልያስን፥ “ጠላቴ ሆይ! አገኘኸኝን?” አለው። እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “አግኝቼሃለሁ፤ ታስቈጣው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አድርገሃልና እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ኤርምያስ 41:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ፥ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ዐብረውት ከነበሩት ስምንት ሰዎች ጋራ ከዮሐናን አመለጠ፤ ሸሽቶም ወደ አሞናውያን ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስማኤልና ስምንት ሰዎቹ ግን ከዮሐናን እጅ አምልጠው ወደ ዐሞን ምድር ኰበለሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ። |
አክዓብም ኤልያስን፥ “ጠላቴ ሆይ! አገኘኸኝን?” አለው። እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “አግኝቼሃለሁ፤ ታስቈጣው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አድርገሃልና እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በሰባተኛው ወር ግን የመንግሥት ዘር የነበረ የኤልሴማ ልጅ የናታንዩ ልጅ እስማኤል መጣ፤ ከእርሱም ጋር ዐሥር ሰዎች ነበሩ፤ ጎዶልያንም መታው፤ ሞተም፤ ከእርሱም ጋር በመሴፋ የነበሩትን አይሁድንና ከለዳውያንንም ገደላቸው።
የናታንያም ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በሀገሩ ላይ የሾመውን ገደሉ።
አረማውያንም እፉኝቱ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል፤ ከባሕር እንኳ በደኅና ቢወጣም በሕይወት ይኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ፍርድ አልተወውም” አሉ።
ዳዊትም ሄዶ የአጥቢያ ኮከብ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግመኛም በማግሥቱ መታቸው፤ ከእነርሱም በግመል ተቀምጠው ከሸሹት አራት መቶ ጐልማሶች በቀር አንድም ያመለጠ የለም።