የይሁዳም ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፥ ከብላቴኖቹም፥ ከአለቆቹም፥ ከጃንደረቦቹም ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ያዘው።
ኤርምያስ 38:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል፤ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ባትሰጥ ግን ይህች ከተማ ለባቢሎናውያን ዐልፋ ትሰጣለች፤ እነርሱም ያቃጥሏታል፤ አንተም ራስህ ከእጃቸው አታመልጥም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል አንተም ከእጃቸው አታመልጥም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእነርሱ እጅህን ባትሰጥ ግን ይህች ከተማ ለባቢሎናውያን ተላልፋ ትሰጣለች፤ እነርሱም ያቃጥሉአታል፤ አንተም ማምለጥ አትችልም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል አንተም ከእጃቸው አታመልጥም አለው። |
የይሁዳም ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፥ ከብላቴኖቹም፥ ከአለቆቹም፥ ከጃንደረቦቹም ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ያዘው።
ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁና፤ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ትሰጣለች፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።”
“ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከንደነፆር የማይገዛውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”
የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ማርጋናሳር፥ ሳማጎት፥ ናቡሳኮር፥ ናቡሰሪስ፥ ናግራጎስናሴር፥ ረብማግ፥ ኔርጋል ሴሪአጼር፥ ከቀሩት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።
መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል፤ ወደ ከለዳውያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ሆኖም አያያትም፤ በዚያም ይሞታል።
እርሱ ግን በእርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረሶችንና ብዙንም ሕዝብ ይሰጡት ዘንድ መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከናወንለት ይሆን? ይህንስ ያደረገ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንንስ ያፈረሰ ያመልጣልን?