ኤርምያስ 34:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎንም ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳን ከተሞች ሁሉ፥ ለኪሶንና አዚቃንም ይወጋ ነበር። እነዚህ የተመሸጉ ከተሞች በይሁዳ ከተሞች መካከል ቀርተው ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳ ከተሞች ለኪሶንና ዓዜቃን እየወጋ ነበር፤ ከተመሸጉት የይሁዳ ከተሞችም የቀሩት እነዚሁ ብቻ ነበሩና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም የተናገረው የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ የቀሩትን ለኪሶንና ዓዜቃንን በወጋ ጊዜ ነበር፤ ከተመሸጉት ከይሁዳ ከተሞች መካከል የተረፉት እነዚህ ብቻ ነበሩና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት በኢየሩሳሌም ከዚያም አልፎ ላኪሽና ዐዜቃ ተብለው በሚጠሩት፥ በይሁዳ ቀርተው በነበሩት የመጨረሻ የተመሸጉ ከተሞች ላይ አደጋ እየጣለ ነበር። |
የአሦርም ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው፤ እርሱም በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛዪቱ ኵሬ መስኖ አጠገብ ቆመ።
በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሄደው ወደሚያጥኑላቸው፥ በመከራቸው ጊዜ ከቶ ወደማያድኗቸው አማልክት ይጮኻሉ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ፥ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ፥ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦
በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና፦ በሀገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፤ ጮኻችሁም፦ ሁላችሁ ተሰብሰቡ፤ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።
“ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።
በለኪሶ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሰረገላውን ለፈረስ እሰሪ፥ እርስዋ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፥ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።
በሀገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ፥ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ሁሉ ያጠፋሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ፥ በደጆች ሁሉ ያስጨንቅሃል።
ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥
አምስቱም የኢያቡሴዎን ነገሥት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የላኪስ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፤ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።