ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ሰፈረባት፤ በዙሪያዋም ዕርድ ሠራባት።
ኤርምያስ 32:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤርምያስም በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤርምያስም በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ ተዘግቶበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩም ኤርምያስ በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በእስር ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊት በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ከበባ ያደረገበት ጊዜ ነበር፤ እኔም በዚያን ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ተዘግቶብኝ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፥ ነቢዩም ኤርምያስ በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር። |
ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ሰፈረባት፤ በዙሪያዋም ዕርድ ሠራባት።
የኡዛይ ልጅ ፋልል በማዕዘኑ አንጻር ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ። ከእርሱም በኋላ የፋሮስ ልጅ ፈዳያ ሠራ።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ ብሎ አስጠብቆት ነበርና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይቺን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ይይዛታል ብለህ ስለምን ትንቢት ትናገራለህ?
እንደ እግዚአብሔርም ቃል የአጎቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወደ አለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፥ “በብንያም ሀገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ፤ የመግዛትና የመውረስ መብቱ የአንተ ነውና፥ አንተ ታላቃችን ነህና፤ ለአንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወቅሁ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ፥ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ፥ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦
ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፤ ኤርምያስንም በግዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖሩት፤ እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከውጪ ጋጋሪዎች እያመጡ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በግዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀምጦ ነበር።
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በግዞት ቤትም አደባባይ ወደ ነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤርምያስንም በገመድ አወረዱት። በጕድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።