ኤርምያስ 30:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ የእግዚአብሔር ቍጣ ለመቅሠፍት ወጥቶአል፤ የመዓቱንም ጥፋት በኃጥኣን ራስ ላይ አምጥቶአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ የእግዚአብሔር ማዕበል፣ በቍጣ ይነሣል፤ የሚገለባብጥም ዐውሎ ነፋስ፣ በክፉዎች ዐናት ላይ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የጌታ ዐውሎ ነፋስ! ቁጣው ወጥቶአል፥ ጥቅል ዐውሎ ነፍስ፤ እርሱም በክፉዎች ራስ ላይ ይወርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለው የእግዚአብሔር ቊጣ እንደ ኀይለኛ ነፋስ እየተገለባበጠ በክፉዎች ራስ ላይ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፥ እርሱም ቍጣው፥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፋስ ወጥቶአል፥ የዓመፀኞችንም ራስ ይገለባብጣል። |
ጭቅጭቅ ድንገት በመጣባችሁ ጊዜ፥ እንደዚሁም ጥፋታችሁ እንደ ዓውሎ ነፋስ በመጣባችሁ ጊዜ፥ ችግርና ምርኮ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ እኔ ከዚያ አለሁ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ክፉ ነገር ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፤ ጽኑም ዐውሎ ነፋስ ከምድር ዳርቻ ይነሣል።
በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይሏቸዋል፦ በምድረ በዳ የሚያስት ጋኔን አለ፤ የሕዝቤ ሴት ልጅ መንገድም ለንጽሕና ወይም ለቅድስና አይደለም።
ላሜድ። እናንተ መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ! በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደ ተደረገው እንደ እኔ ቍስል የሚመስል ቍስል እንዳለ ተመልከቱ፤ እዩም።
እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።