ኤርምያስ 28:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሰተኛው ነቢይ ሐናንያም በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነቢዩ ሐናንያም በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ። |
እነሆ ከምላሳቸው ትንቢትን አውጥተው፦ እርሱ የእግዚአብሔር ሸክም ነው በሚሉ ነቢያት ላይ ነኝ፤ ይላል እግዚአብሔር፤
ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ፥ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ሐሰተኛው ነቢይ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስወግድሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ዐመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ” አለው።
ነቢዩ ኤርምያስ ወደ ተረፉት የምርኮ ሽማግሌዎች፥ ወደ ካህናቱም፥ ወደ ሐሰተኞች ነቢያቱም፥ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃል ይህ ነው።
ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።
ነገር ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን ቃል በስሜ የሚናገር ነቢይ፥ በሌላ አማልክት ስም የሚናገር ነቢይም፥ እርሱ ይገደል።