ኤርምያስ 27:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስላልወሰዳቸው ዓምዶች፥ ስለ ባሕሩም፥ ስለ መቀመጫዎቹም፥ በዚች ከተማ ስለ ቀሩት ዕቃዎች ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህች ከተማ ስለ ቀሩት ዐምዶች፣ ከናስ ስለ ተሠራው ትልቁ ገንዳ፣ ስለ ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎችና ስለ ሌሎቹም ዕቃዎች እንዲህ ይላልና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህች ከተማ ቀርተው ስለ ተተዉት ዕቃዎች፥ ስለ ዓምዶቹ፥ ስለ ኩሬውም፥ ስለ መቀመጫዎቹም፥ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳ ንጉሥ የሆነውን የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ታላላቅ ሰዎች ጋር ወደ ባቢሎን ማርኮ በወሰደው ጊዜ ዐምዶችን፥ ከነሐስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ፥ የብረት ማስቀመጫዎችንና ሌሎችንም የቤተ መቅደስ ዕቃዎች በኢየሩሳሌም ትቶአቸው ሄዶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ከበርቴዎች ሁሉ ማርኮ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ ስላልወሰዳቸው ዓምዶች ስለ ኵሬውም ስለ መቀመጫዎቹም በዚህችም ከተማ ስለ ቀረች ዕቃ ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ |
ዐሥርም የናስ መቀመጫዎችን ሠራ፤ የአንዱም መቀመጫ ርዝመት አራት ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ ነበረ።
ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የነበሩትን የናስ ዓምዶች፥ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናስ ኵሬዎች ሰባበሩ፤ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የናስም ጕልላት ነበረበት፤ የጕልላቱም ርዝመት ሦስት ክንድ ነበረ፥ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው የናስ መርበብና ሮማኖች ነበሩ፤ እንዲሁም ደግሞ በሁለተኛው ዓምድ ላይ መርበብ ነበረበት።
የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንም ቤት መዝገብ፥ የአለቆቹንም ቤት መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
ዮድ። አስጨናቂው በምኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።