አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ፥ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር።
ኤርምያስ 26:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም የቂርያትይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኡርያ ይባል ነበር፤ በዚችም ከተማ፥ በዚችም ምድር ላይ እንደ ኤርምያስ ቃል ሁሉ ትንቢት ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም የቂርያትይዓይሪም ሰው፣ የሸማያ ልጅ ኦርዮ፣ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ ሌላው ሰው ነበር፤ እርሱም እንደ ኤርምያስ በዚህች ከተማና በዚህ ምድር ላይ ትንቢት ተናግሮ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም በጌታ ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የቂርያት-ይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፥ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ እንደ ኤርምያስ ቃላት ሁሉ ትንቢት ተናገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቂርያትይዓሪም የሚኖር የሸማያ ልጅ ኡሪያ የተባለ ሌላም ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ልክ እንደ ኤርምያስ በዚህች ከተማና በዚህች ምድር ላይ ጥፋት እንደሚመጣ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የቂርያትይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፥ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ እንደ ኤርምያስ ቃል ሁሉ ትንቢት ተናገረ። |
አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ፥ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር።
ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፤ ተግሣጼን አልተቀበላችሁም፤ ሰይፋችሁ እንደሚሰብር አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል፤ በዚህም አልፈራችሁኝም።
ቴቆ፥ ኤፍራታ፥ ይኽችውም ቤተ ልሔም ናት፤ ፋጎርም፥ ኤጣንም፥ ቁሎን፥ ጠጦንም፥ ሶብሄም፥ ቃሬም፥ ጌሌም፥ ኤቴር፥ መነኮም፥ ዐሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው፥ ቅርያትበኣል፥ ይኽችውም የኢያርም ከተማ ናት፤ ሶቤታ፥ ሁለቱ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
ድንበሩም ወደ ባሕር ሄደ፤ በቤቶሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ አዜብ ዞረ፤ መውጫውም ቂርያታርም በምትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያትበኣል ነበረ፤ ይህ በባሕር በኩል ነበረ።
የእስራኤልም ልጆች ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮትና ኢያሪም ነበሩ።
በቂርያትይዓሪምም ወደ ተቀመጡት ሰዎች መልእክተኞችን ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰዋል፤ ወርዳችሁም ወደ እናንተ ውሰዱአት” አሉ።
ታቦቲቱም በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠችበት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፤ ሃያ ዓመትም ሆነ፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግዚአብሔርን ተከተለ።