የእግዚአብሔርም መልአክ ኢየሩሳሌምን ያጠፋት ዘንድ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ከክፉው ነገር ይቅር አላት፤ ሕዝቡንም የሚያጠፋውን መልአክ፥ “እንግዲህ በቃህ፤ እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበረ።
ኤርምያስ 26:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ እግዚአብሔርን አልፈሩምን? ወደ እግዚአብሔርስ አልተማለሉምን? እግዚአብሔርስ የተናገረባቸውን ክፉ ነገር አይተዉምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ታዲያ፣ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስም ሆነ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ገደሉትን? ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን ፈርቶ ምሕረት አልለመነምን? እግዚአብሔርስ በእነርሱ ላይ ለማምጣት ያሰበውን ቅጣት አልተወምን? በራሳችን ላይ እኮ ታላቅ ጥፋት እያመጣን ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ ንጉሡ ጌታን አልፈራን? ወደ ጌታስ አልተማጠነምን? ጌታስ በእነርሱ ላይ የተናገረውን ክፉ ነገር አልተወምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ ንጉሥ ሕዝቅያስና የይሁዳ ሕዝብ ሚክያስ እንዲገደል አደረጉን? አይደለም! ይልቁንም ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን በመፍራት ምሕረት እንዲያደርግለት ተማጠነ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ሊያመጣ ዐቅዶት የነበረውን መቅሠፍት መለሰ፤ እኛ ግን አሁን አሠቃቂ የሆነ መቅሠፍት በራሳችን ላይ ለማምጣት ተዘጋጅተናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ እግዚአብሔርን አልፈሩምን? ወደ እግዚአብሔርስ አልተማለሉምን? እግዚአብሔርስ የተናገረባቸውን ክፉ ነገር አይተውምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን። |
የእግዚአብሔርም መልአክ ኢየሩሳሌምን ያጠፋት ዘንድ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ከክፉው ነገር ይቅር አላት፤ ሕዝቡንም የሚያጠፋውን መልአክ፥ “እንግዲህ በቃህ፤ እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበረ።
“በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቁ፥ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ ተገኘው የመጽሐፍ ቃል ስለእኔ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ስለቀሩትም እግዚአብሔርን ጠይቁ” ብሎ አዘዛቸው።
እነሆ፥ እግዚአብሔር በምድር በሚኖሩት ላይ ከመቅደሱ መቅሠፍቱን ያመጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፤ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።
ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፥ ስለዚህ ለቀረው ቅሬታ ጸልይ” አሉት።
ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነቱ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚች ከተማ፥ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በርግጥ ዕወቁ።”
ምናልባት እያንዳንዳቸው ይሰሙ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ስለ ሥራቸው ክፋት ያሰብሁባቸውን ክፉ ነገር እተዋለሁ።”
“አሁንም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከይሁዳ ወገን መካከል ቅሬታ እንዳይቀርላችሁ፥ ወንድንና ሴትን፥ ብላቴናንና የሚጠባ ሕፃንን ከመካከላችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?
የእነዚህ ኃጥኣን ጥናዎቻቸው በሰውነታቸው ጥፋት ተቀድሰዋልና፤ የተጠፈጠፈ ሰሌዳ አድርጋቸው፤ ለመሠዊያ መለበጫም ይሁኑ፤ በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋቸዋልና የተቀደሱ ናቸው፤ ለእስራኤልም ልጆች ምልክት ይሆናሉ።”
ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችኋል።