ኤርምያስ 25:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ጥፋት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉም ጋር ይፋረዳል፤ ኀጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከሕዝቦች ጋራ ይፋረዳልና፣ ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ያስተጋባል፤ በሰው ሁሉ ላይ ፍርድን ያመጣል፤ ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል’ ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ከአሕዛብ ጋር ሙግት አለውና ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሕዝቡን በሚገሥጽበት ጊዜ የሚያሰማው ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል፤ በሕዝቦች ሁሉ ላይ ይፈርዳል፤ ክፉዎችንም በሞት ይቀጣል፤’ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፥ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። |
የእግዚአብሔር ቍጣ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ነውና፤ መቅሠፍቱም ያጠፋቸውና ለጦር ይሰጣቸው ዘንድ በቍጥራቸው ልክ ነው።
ምድርም ሁሉ በእግዚአብሔር እሳት ሰውም ሁሉ በሰይፉ ይፈረድባቸዋል፤ በእግዚአብሔርም ተቀሥፈው የሞቱት ይበዛሉ።
እነሆ ከእግዚአብሔር ዘንድ ንውጽውጽታ ይመጣል፤ ኃጥኣንን ያነዋውጣቸውና ይገለብጣቸው ዘንድ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ የዐመፀኞችን ራስ ይገለባብጣል።
ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ እነሆ ክፉ ነገርን አመጣለሁና አትፈልጋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።”
በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍም፥ የበረዶም ድንጋይ፥ እሳትና ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ፥ ከእርሱም ጋር በአሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ።
ኤፍሬም ግን ክብርንና ከንቱ ነገርን የሚያሳድድ ክፉ ጋኔን ነው። ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፤ ከአሦርም ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ ምሕረትም ያደርጉለት ዘንድ ወደ ግብፅ ዘይትን ይልካል።
እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ምሕረት፥ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚኖሩትን ይወቅሳልና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
አሕዛብን ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል በተበተኑበትና ምድሬን በተካፈሉበት በዚያ ስለ ወገኖች ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል እወቅሳቸዋለሁ።
ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።