Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 25:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እግዚአብሔር ከሕዝቦች ጋራ ይፋረዳልና፣ ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ያስተጋባል፤ በሰው ሁሉ ላይ ፍርድን ያመጣል፤ ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል’ ” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ጌታ ከአሕዛብ ጋር ሙግት አለውና ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እግዚአብሔር ሕዝቡን በሚገሥጽበት ጊዜ የሚያሰማው ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል፤ በሕዝቦች ሁሉ ላይ ይፈርዳል፤ ክፉዎችንም በሞት ይቀጣል፤’ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሕ​ዛብ ጋር ክር​ክር አለ​ውና ጥፋት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉም ጋር ይፋ​ረ​ዳል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፥ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 25:31
14 Referencias Cruzadas  

ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፤ መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ።


እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ተቈጥቷል፤ ቍጣውም በሰራዊታቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ፈጽሞ ያጠፋቸዋል፤ ለዕርድም አሳልፎ ይሰጣቸዋል።


እግዚአብሔር የበቀል ቀን፣ ስለ ጽዮንም የሚሟገትበት ዓመት አለውና።


በእሳትና በሰይፍ፣ እግዚአብሔር ፍርዱን በሰው ሁሉ ላይ ያመጣል፤ በእግዚአብሔር ሰይፍ የሚታረዱት ብዙ ይሆናሉ።


‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በርግጥ ቍጣው ከእኔ ርቋል’ ትያለሽ። እኔ ግን እፈርድብሻለሁ፤ ‘ኀጢአት አልሠራሁም’ ብለሻልና።


እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፣ በቍጣ ይነሣል፤ ብርቱም ማዕበል፣ የክፉዎችን ራስ ይመታል።


ታዲያ፣ ለራስህ ታላቅ ነገር ትሻለህን? በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ጥፋት አመጣለሁና አትፈልገው፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ሁሉ ሕይወትህ እንዲተርፍልህ አደርጋለሁ።’ ”


ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደመና ቀን፣ ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።


በቸነፈርና በደም መፋሰስ እፈርድበታለሁ፤ የዝናብ ዶፍ፣ የበረዶ ድንጋይ፣ የሚያቃጥል ድኝ፣ በርሱና በወታደሮቹ፣ ከርሱም ጋራ ባሉት ሕዝቦች ላይ አወርዳለሁ።


እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።


እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤ ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።


አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ወደ ኢዮሣፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ ስለ ርስቴ፣ ስለ ሕዝቤ፣ ስለ እስራኤል፣ በዚያ ልፈርድባቸው እገባለሁ፤ ምድሬን ከፋፍለዋል፤ ሕዝቤንም በሕዝቦች መካከል በታትነዋልና።


“ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ክስ አድምጡ፤ እናንተ የምድር ጽኑ መሠረቶችም፣ ስሙ፤ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋራ ክርክር አለውና፤ ከእስራኤልም ጋራ ይፋረዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos