ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። የኬልቀዶን መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ጠፍተዋልና፤ እንግዲህም ከኬጤዎን ሀገር አይመጡምና ማርከውም ይወስዱአቸዋልና።
ኤርምያስ 25:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጢሮስንም ነገሥታት ሁሉ፥ የሲዶናንም ነገሥታት ሁሉ፥ በባሕር ማዶ ያሉ የደሴት ነገሥታትንም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጢሮስንና የሲዶናን ነገሥታት ሁሉ፣ ከባሕሩ ማዶ ያሉ የጠረፍ ምድር ነገሥታትን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጤሮስን ነገሥታትም ሁሉ፥ የሲዶናን ነገሥታትም ሁሉ፥ በባሕር ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትንም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጤሮስን ነገሥታትም ሁሉ፥ የሲዶናን ነገሥታትም ሁሉ፥ በባህር ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትንም፥ |
ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። የኬልቀዶን መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ጠፍተዋልና፤ እንግዲህም ከኬጤዎን ሀገር አይመጡምና ማርከውም ይወስዱአቸዋልና።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ጢሮስ እንደ አንድ ንጉሥ ዘመን ወይም እንደ አንድ ሰው ዘመን ሰባ ዓመት ያህል የተረሳች ትሆናለች፤ ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢሮስ በጋለሞታ ዘፈን እንደሚሆን እንዲሁ ይሆናል።
ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባሕር ምሽግ፥ “አላማጥሁም፥ አልወለድሁም፤ ጐበዛዝትንም አላሳደግሁም፥ ደናግልንም አላሳደግሁም” ብሎ ተናግሮአልና እፈሪ።
ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ፥ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፥ ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ላክ።”
አሕዛብ ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፥ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፤ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ።
ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ታጠፋ ዘንድ፥ ጢሮስንና ሲዶናን የቀሩትንም ረዳቶቻቸውን ታጠፋ ዘንድ ስለምትመጣው ቀን ነው፤ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንንና በከፍቶር ደሴት የቀሩትን ያጠፋልና።
ኀይልሽና ዋጋሽ፥ ንግድሽም፥ መርከበኞችሽም፥ መርከብ መሪዎችሽም፥ ሰባራሽን የሚጠግኑ ነጋዴዎችሽም፥ በአንቺም ዘንድ ያሉ ሰልፈኞችሽ ሁሉ በውስጥሽ ከአሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በወደቅሽበት ቀን በባሕር ውስጥ ይጠፋሉ።
“የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊቱን በጢሮስ ላይ ጽኑ ሥራን አሠራቸው፤ ራስ ሁሉ የተላጨ፥ ጫንቃም ሁሉ የተላጠ ሆኖአል፤ ነገር ግን በላይዋ ስለ አሠራው ሥራ እርሱና ሠራዊቱ ከጢሮስ ደመወዝ አልተቀበሉም።
ከአልተገረዙና ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተኝተዋል፤ የሰሜን አለቆች ሁሉ፥ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፤ በኀይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሀት አፍረዋል፤ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ያልተገረዙት ተኝተዋል፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር ቅጣታቸውን ተሸክመዋል።