ኤርምያስ 25:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፤ አስቀሎናንም፥ ጋዛንም፥ አቃሮንንም፥ የአዛጦንንም ቅሬታ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ የሚኖሩትን ድብልቅ ሕዝብ ሁሉ፣ የዖፅ ምድር ነገሥታትን ሁሉ፣ በአስቀሎና፣ በጋዛ፣ በአቃሮንና በአዛጦንም ሕዝብ ቅሬታ ያሉትን የፍልስጥኤም ነገሥታት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዑፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዛጦንንም ትሩፍ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዛጦንንም ቅሬታ፥ |
አውስጢድ በሚባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹሕና ጻድቅ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።
ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ፥ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፥ ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ላክ።”
ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ፥ በመካከልዋም በተቀላቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በመዝገቦችዋ ላይ አለ፤ ይበተናሉም።
ሣን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፥ ሐሤትም አድርጊ፤ የእግዚአብሔር ጽዋ ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋልና፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ፥ ትራቆቻለሽም።
ኢትዮጵያና ፉጥ፥ ሉድም፥ ዓረብም ሁሉ፥ ኩብም፤ ሊብያም፤ ቀርጤስም የተደባለቀ ሕዝብም ሁሉ፥ ቃል ኪዳንንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።
ይሁዳም ጋዛንና አውራጃዋን፥ አስቀሎናንና አውራጃዋን፥ አቃሮንንና አውራጃዋን፥ አዛጦንንና አውራጃዋን አልወረሳትም።
ፍልስጥኤማውያንም ስለ በደል መባእ ለእግዚአብሔር ያቀረቡአቸው የሰውነታቸው ምሳሌ የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፦ አንዲቱ ለአዛጦን፥ አንዲቱም ለጋዛ፥ አንዲቱም ለአስቀሎና፥ አንዲቱም ለጌት፥ አንዲቱም ለአቃሮን።