አሁንም ሂድ፤ ይህንም ሕዝብ ወደ ነገርሁህ ቦታ ምራ፤ እነሆ፥ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ ነገር ግን በምጐበኝበት ቀን ኀጢአታቸውን አመጣባቸዋለሁ” አለው።
ኤርምያስ 23:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፥ “በጎችን በትናችኋል፤ አባርራችኋቸውማል፥ አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ! እንደ ሥራችሁ ክፋት እጐበኛችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፤ “መንጋዬን ስለ በተናችሁ፣ ስላባረራችሁና ተገቢውን ጥንቃቄ ስላላደረጋችሁላቸው፣ ለክፋታችሁ ተገቢውን ቅጣት አመጣባችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸዋልም አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ ስለ ክፉ ሥራችሁ እጐበኛችኋለሁ፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሕዝቡ ጠባቂዎች መሆን ስለሚገባቸው መሪዎች እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን እንደሚገባ አልጠበቃችሁም፤ ይልቁንም አሳዳችሁ በተናችሁ፤ ስለዚህ ስለ ፈጸማችሁት ክፋት ሁሉ እቀጣችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፥ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
አሁንም ሂድ፤ ይህንም ሕዝብ ወደ ነገርሁህ ቦታ ምራ፤ እነሆ፥ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ ነገር ግን በምጐበኝበት ቀን ኀጢአታቸውን አመጣባቸዋለሁ” አለው።
እረኞች አእምሮአቸውን አጥተዋልና፥ እግዚአብሔርንም አልፈለጉትምና፤ ስለዚህም መሰማሪያውን አላወቁም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በመዓት እጐበኛቸዋለሁ፤ ጐበዛዝቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤
ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች።
ኢየሩሳሌም ሆይ! ዐይንሽን አንሥተሽ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቺ፤ ለአንቺ የሰጠሁሽ መንጋ፤ የክብር በጎችሽ ወዴት አሉ?
እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ፤ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።”
የዳዊት ቤት ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይነድድና ማንም ሳያጠፋው እንዳያቃጥል፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።
እግዚአብሔርም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኵሰት ይታገሥ ዘንድ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ፥ በረሃና መረገሚያ ሆናለች፤ እስከ ዛሬም የሚኖርባት የለም።
አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፤ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ፤ ይላል እግዚአብሔር።
እኔን ረስታ ወዳጆችዋን እየተከተለች፥ በጕትቾችዋና በጌጥዋም እያጌጠች ለበኣሊም የሠዋችበትን ወራት እበቀልባታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ።
ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነድዶአል፥ አውራ ፍየሎችንም እቀጣለሁ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በሰልፍም ውስጥ እንዳለ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።
እነሆ፥ በአገሩ ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፣ እርሱም የጠፋውን አያስብም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፣ የዳነውንም አይቀልብም፥ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል።
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።