La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 23:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ንው​ጽ​ው​ጽታ ይመ​ጣል፤ ኃጥ​ኣ​ንን ያነ​ዋ​ው​ጣ​ቸ​ውና ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸው ዘንድ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል፤ የዐ​መ​ፀ​ኞ​ችን ራስ ይገ​ለ​ባ​ብ​ጣል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፣ በቍጣ ይነሣል፤ ብርቱም ማዕበል፣ የክፉዎችን ራስ ይመታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ የጌታ ዐውሎ ነፋስ! ቁጣው ወጥቶአል፥ ጥቅል ዐውሎ ነፍስ፤ እርሱም በክፉዎች ራስ ላይ ይወርዳል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእግዚአብሔር ቊጣ በክፉዎች ራስ ላይ እንደሚተም ማዕበልና እንደ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ሲወርድ ተመልከት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፥ እርሱም ቍጣው፥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፍስ ወጥቶአል፥ የዓመፀኞችን ራስ ይገለባብጣል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 23:19
19 Referencias Cruzadas  

ኀይ​ሌን ወደ አንተ አስ​ጠ​ጋ​ለሁ፥ አንተ አም​ላ​ኬና መጠ​ጊ​ያዬ ነህና።


ጭቅጭቅ ድንገት በመጣባችሁ ጊዜ፥ እንደዚሁም ጥፋታችሁ እንደ ዓውሎ ነፋስ በመጣባችሁ ጊዜ፥ ችግርና ምርኮ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ እኔ ከዚያ አለሁ።


ኃጥእ እንደ ዐውሎ ነፋስ ኅልፈት ይጠፋል፤ ጻድቅ ግን ተሰውሮ ለዘለዓለም ይድናል።


ስለ ምድረ በዳ የተ​ነ​ገረ ቃል፤ ዐውሎ ነፋስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ፥ እን​ዲሁ ከሚ​ያ​ስ​ፈራ ሀገር ከም​ድረ በዳ ይመ​ጣል።


በእ​ር​ሱም ላይ ዛፉ​ንና ሣሩን፥ የማ​ይ​ቈ​ጠር ሌላ​ው​ንም ብዙ ፍጥ​ረት የፈ​ጠረ እርሱ ነው። ነፋ​ስም በነ​ፈ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይደ​ር​ቃሉ፤ ዐውሎ ነፋ​ስም እንደ ገለባ ይጠ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሕ​ዛብ ጋር ክር​ክር አለ​ውና ጥፋት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉም ጋር ይፋ​ረ​ዳል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ክፉ ነገር ከሕ​ዝብ ወደ ሕዝብ ይወ​ጣል፤ ጽኑም ዐውሎ ነፋስ ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣል።


እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ለመ​ቅ​ሠ​ፍት ወጥ​ቶ​አል፤ የመ​ዓ​ቱ​ንም ጥፋት በኃ​ጥ​ኣን ራስ ላይ አም​ጥ​ቶ​አል፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የል​ቡን አሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ታው​ቁ​ታ​ላ​ችሁ።


በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝ​ብና ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ይሏ​ቸ​ዋል፦ በም​ድረ በዳ የሚ​ያ​ስት ጋኔን አለ፤ የሕ​ዝቤ ሴት ልጅ መን​ገ​ድም ለን​ጽ​ሕና ወይም ለቅ​ድ​ስና አይ​ደ​ለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በባ​ቢ​ሎን ላይና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልና የሚ​ያ​ጠፋ ነፋ​ስን አስ​ነ​ሣ​ለሁ።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከሰ​ሜን በኩል ዐውሎ ነፋ​ስና ታላቅ ደመና፥ የሚ​በ​ር​ቅም እሳት መጣ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ልም በእ​ሳቱ ውስጥ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ ነገር ነበረ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ዓቴ በዐ​ውሎ ነፋስ እሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ያጠ​ፋ​ውም ዘንድ በቍ​ጣዬ የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ፥ በመ​ዓ​ቴም ታላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ር​ዳ​ለሁ።


በራባ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በጦ​ር​ነት ቀን በጩ​ኸት መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋን ትበ​ላ​ለች፤ በፍ​ጻ​ሜ​ዋም ቀን ትና​ወ​ጣ​ለች።


ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፣ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።


እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።