እግዚአብሔርም ነቢዩ ናታንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እርሱም መጥቶ አለው፥ “በአንድ ከተማ አንዱ ባለጠጋ፥ አንዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።
ኤርምያስ 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ፤ በዚያም ይህን ቃል ተናገር፥ እንዲህም በል፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት ውረድ፤ ይህንም መልእክት በዚያ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ አለ፦ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ በዚያም ይህን ቃል ተናገር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የዳዊት ዘር ወደ ሆነው ወደ ይሁዳ ቤተ መንግሥት እንድወርድና በዚያም ለንጉሡ፥ ለመኳንንቱና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እኔ የምነግራቸውን ቃል እንዲያዳምጡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው አለኝ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ በዚያም ይህን ቃል ተናገር፥ |
እግዚአብሔርም ነቢዩ ናታንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እርሱም መጥቶ አለው፥ “በአንድ ከተማ አንዱ ባለጠጋ፥ አንዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።
እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
በዳዊት ዙፋን የምትቀመጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ! አንተና አገልጋዮችህ በእነዚህም በሮች የሚገባ ሕዝብህ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድ፤ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይች ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፋ ትሰጣለች፤ ይይዛታል፤ በእሳትም ያቃጥላታል።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።