አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፥ አቤቱ፥ ዐይንህን ክፈትና እይ፤ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ስማ።
ኤርምያስ 18:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አቤቱ! አድምጠኝ፤ የክርክሬንም ቃል ስማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማኝ፤ ባላንጣዎቼ የሚሉትን አድምጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! አድምጠኝ፥ ጠላቶቼ ምን እደሚሉ ስማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እንዲህ በማለት ጸለይኩ “እግዚአብሔር ሆይ! ልመናዬን ስማ፤ ጠላቶቼም በእኔ ላይ የሚናገሩትን ክፉ ነገር አድምጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ አድምጠኝ፥ የክርክሬንም ቃል ስማ። |
አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፥ አቤቱ፥ ዐይንህን ክፈትና እይ፤ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ስማ።
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
ለሰውነቴ ጕድጓድን ቈፍረዋል፤ በውኑ በመልካም ፈንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ፥ ቍጣህንም ከእነርሱ ትመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ።
አቤቱ! ጽድቅን የምትፈትን ኵላሊትንና ልብን የምትመረምር የሠራዊት ጌታ ሆይ! ክርክሬን ገልጬልሃለሁና ፍረድልኝ።