ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
ኤርምያስ 17:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም በላቸው፥ “በእነዚህ በሮች የምትገቡ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፥ ይሁዳም ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም በላቸው፤ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ነገሥታት ሆይ፤ የይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም በላቸው፦ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ፥ የይሁዳ ነገሥታት ሆይ! ይሁዳም ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁሉ፥ የጌታን ቃል ስሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የምነግርህንም ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የይሁዳ ነገሥታትና ሕዝብ! እንዲሁም በእነዚህ ቅጽር በሮች የምትገቡ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም በላቸው፦ በእነዚህ በሮች የምትገቡ፥ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፥ ይሁዳም ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። |
ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፥ “ሂድ፤ የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝብህ ልጆች በር በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም።”
“የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ስፍራ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ የሰማውም ሰው ሁሉ ይደነግጣል፤ ጆሮዎቹንም ይይዛል።
ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነዋልና፥ የይሁዳም ነገሥታት ይህን ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተዋልና፥
በዳዊት ዙፋን የምትቀመጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ! አንተና አገልጋዮችህ በእነዚህም በሮች የሚገባ ሕዝብህ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኞችንም የምታስጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።