ለበዓልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።
ኤርምያስ 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገርን ስለ ምን እግዚአብሔር ተናገረብን? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ኀጢአት ምንድን ነው? ቢሉህ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ሁሉ ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ ሰዎቹ፣ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ ለምን ዐወጀ? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኀጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ቢጠይቁህ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃላት ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ‘ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገርን ለምን ጌታ ተናገረብን? በደላችንስ ምንድነው? በአምላካችንስ በጌታ ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድነው?’ ቢሉህ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህን ሁሉ በምትነግራቸው ጊዜ ‘እግዚአብሔር በእኛ ላይ ይህን የሚያኽል ከባድ ጥፋት ለምን ወሰነብን? ምን በደልን? በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊትስ የሠራነው ኃጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ይጠይቁሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገርን ስለ ምን እግዚአብሔር ተናገረብን? በደላችንስ ምንድር ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድር ነው? ቢሉህ፥ |
ለበዓልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።
በልብሽም፦ እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ? ብትዪ፥ ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ልብስሽ በስተኋላሽ ተገፎአል፤ ተረከዝሽም ተገልጦአል።
አንቺስ፦ አልረከስሁም፤ በዓሊምንም አልተከተልሁም፤ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፤ ያደረግሽውንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመንገዶች ትጮኻለች፤
ይህም የሆነው ያስቈጡኝ ዘንድ ስላደረጉት ክፋት፥ እነርሱና አባቶቻቸው ለማያውቁአቸው ለሌሎች አማልክት ያጥኑ ዘንድ፥ ያመልኳቸውም ዘንድ ስለሄዱ ነው።
እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ፥ “አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደረገብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋችሁኝ፥ በሀገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ ሀገር ለሌሎች ሰዎች ትገዛላችሁ” ትላቸዋለህ።
ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው እንዳይቀመጥባቸው አጠፋቸዋለሁ።