እግዚአብሔርም ተስፋሽን አስቈርጦሻልና፥ በእርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።
ኤርምያስ 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ስለ ሆነ አራሾች ዐፈሩ፤ ራሳቸውንም ተከናነቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድሪቱ ዝናብ ስለሌለ፣ መሬቱ ተሰነጣጥቋል፤ ገበሬዎችም ዐፍረው፣ ራሳቸውን ተከናንበዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ስለሆነ አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብ ከመጥፋቱ የተነሣ፥ ምድር ትደርቃለች፤ ገበሬዎችም ተስፋ በመቊረጥ፥ በሐዘን ራሳቸውን ይሸፍናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ስለሆነ አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ። |
እግዚአብሔርም ተስፋሽን አስቈርጦሻልና፥ በእርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።
ለጕስቍልናሽ ከብዙዎች እረኞች ጋር ኖርሽ የአመንዝራም ሴት ፊት ነበረብሽ፥ በሁሉም ዘንድ ያለ ኀፍረት ሄድሽ። ስለዚህ የመከርና የበልግ ዝናም ተከለከለ።
መከሩ ከእርሻቸው ጠፍቶአልና ገበሬዎች ስለ ስንዴውና ስለ ገብሱ ዐፈሩ፤ የወይን አትክልተኞችም ስለ ወይኑ አለቀሱ።
የሁለት ወይም የሦስት ከተሞች ሰዎች ወደ አንዲት ከተማ ውኃ ይጠጡ ዘንድ ሄዱ፤ ነገር ግን አልረኩም፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳይዘራባትም፥ እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቍጣውና በመዓቱ እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥