ያዕቆብ 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ ከእናንተም ይሸሻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ ከእናንተም ይሸሻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ |
አሁንም እንደ አባቶቻችሁ አንገታችሁን አታደንድኑ፤ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ስጡ፤ ለዘለዓለምም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣውንም ከእናንተ እንዲመልስ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተገዙ።
እንዲህም አለ፥ “ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደ ምድር እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእግዚአብብሔር ስም የተባረከ ይሁን።”
ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
እርሱም እየፈራና እየተንቀጠቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እንዳደርግ ትሻለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚያም ልታደርገው የሚገባህን ይነግሩሃል” አለው።
የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁአትምና በራሳቸውም ጽድቅ ጸንተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ግን መገዛት ተሳናቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአልና፥ “እኔ ሕያው ነኝ፤ ጕልበትም ሁሉ ለእኔ ይሰግዳል፤ አንደበትም ሁሉ ለእኔ ይገዛል።”
በሥጋ የወለዱን አባቶቻችን የሚቀጡን፥ እኛም የምንፈራቸው ከሆነ፥ እንግዲያ ይልቁን ለመንፈስ አባታችን ልንታዘዝና ልንገዛ በሕይወትም ልንኖር እንዴት ይገባን ይሆን?
ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፤ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።