ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዐይንም ለማየት እንደሚያስጐመጅ፥ መልካምንም እንደሚያሳውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍሬው ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።
ያዕቆብ 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው የሚፈተነው በገዛ ራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። |
ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዐይንም ለማየት እንደሚያስጐመጅ፥ መልካምንም እንደሚያሳውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍሬው ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
ዳዊትም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፤ ከርኵሰቷም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመለሰች።
እንግዲህ ልባቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእነርሱም ነፍሱን ለማዳን የሚችል ማንም እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚልም እንደሌለ ተመልከቱ።
እንግዲህ ያ መልካም ነው ብዬ የማስበው ነገር በውኑ አጥፊ ሆነኝ እላለሁን? አይደለም፤ ነገር ግን ኀጢአት ኀጢአት እንደ ሆነች በታወቀች ጊዜ ሞትን አበዛችብኝ፤ ከዚያም ትእዛዝ የተነሣ ኀጢአተናው እንዲታወቅ፥ ኀጢአትም ተለይታ እንድትታወቅ ኦሪት መልካሙን ከክፉ ልትለይ ተሠርታለች።
ዛሬ የሚባለው ቀን ሳለ ከእናንተ ማንም ቢሆን ወደ ኀጢአት በሚያደርስ ስሕተት እንዳይጸና ሁልጊዜ ሰውነታችሁን መርምሩ።