በዚያም ቀን፦ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠዊያው ይሰነጠቃል፤ በውስጡም ያለው ስብ ይፈስሳል” ብሎ ምልክት ሰጠ።
ኢሳይያስ 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ቢሆን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ምልክትን ለአንተ ለምን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ለምን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከጌታ ከአምላክህ ለምን።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከምድር ጥልቀትም ሆነ ከሰማይ ከፍታ አንድ ምልክት እንዲሰጥህ አምላክህን እግዚአብሔርን ለምን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ቢሆን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ምልክትን ለምን። |
በዚያም ቀን፦ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠዊያው ይሰነጠቃል፤ በውስጡም ያለው ስብ ይፈስሳል” ብሎ ምልክት ሰጠ።
“ይህም ለአንተ ምልክት ይሆንልሃል፤ በዚህ ዓመት የገቦውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላለህ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራለህ፤ ታጭድማለህ፥ ወይንም ትተክላለህ፤ ፍሬውንም ትበላለህ።
“ፈርዖን፦ ተአምራትንና ድንቅን አሳዩኝ ሲላችሁ፥ ወንድምህ አሮንን፦ ‘በትርህን ወስደህ በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ጣላት’ በለው፤ እባብም ትሆናለች።”
“ይህም ምልክት ይሆንሃል፤ በዚህ ዓመት የዘራኸውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላቸሁ፤ ታጭዱማላችሁ፤ ወይንንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።
በእሾህም ፋንታ ጥድ፥ በኵርንችትም ፋንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ የእግዚአብሔርም ስም ለዘለዓለም በማይጠፋ ምልክት ይመሰገናል።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸክላ ሠሪ የሠራውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤
“ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እንደምጐበኛችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር።