የሠራዊቱም አለቃ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰማርያም በንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአርጎብና ከአርያ ጋር መታው፤ ከእርሱም ጋር ከገለዓዳውያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።
ኢሳይያስ 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የአራም ንጉሥ ረአሶን፥ የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ሊይዙአትም አልቻሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዖዝያን የልጅ ልጅ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን፣ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ነገር ግን ድል ሊያደርጓት አልቻሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዖዝያን የልጅ ልጅ፤ የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን፤ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ነገር ግን ድል ሊያደርጓት አልቻሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዖዝያን ልጅ ከኢዮአታም የተወለደው አካዝ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን፥ የሶርያ ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የረማልያ ልጅ ፋቁሔ ጦርነት ማስነሣት ፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ነገር ግን ኢየሩሳሌምን ድል ሊያደርጉአት አልቻሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፥ ሊያሸንፉአትም አልቻሉም። |
የሠራዊቱም አለቃ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰማርያም በንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአርጎብና ከአርያ ጋር መታው፤ ከእርሱም ጋር ከገለዓዳውያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።
በይሁዳ ንጉሥ በዓዛርያስ በአምሳ ሁለተኛው ዓመት የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል ላይ በሰማርያ መንገሥ ጀመረ፤ ሃያ ዓመትም ነገሠ።
ያን ጊዜም የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ሊዋጉ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ አካዝንም ከበቡት፥ ሊያሸንፉት ግን አልቻሉም።
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ።
“እኒህ ሕዝብ በቀስታ በሚሄደው በሰሊሆም ውኃ ቍርጥ ምክርን መከሩ፤ ረአሶንንና የሮሜልዩን ልጅ ያነግሡላቸው ዘንድ ይወዳሉና።
የሶርያም ሰዎች ከገንዘብሽ ብዛት የተነሣ ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ ከአንቺም ጋር አንድ ከሆኑ ከብዙ ሰዎች ጋር ትነግጂ ነበር፤ ነጭ ሐርንና ዕንቍን፥ ቀይ ሐርንና ወርቀ ዘቦን ከርከዴን የሚባል ዕንቍንና ልባንጃም የሚባል ሽቱን ከተርሴስ ያመጡልሽ ነበር፤ ገበያሽንም ረዓሙትና ቆርኮር መሉት።
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስም ዘመን በእስራኤልም ንጉሥ በኢዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታምና በአካዝ በሕዝቅያስም ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው፥ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው፥ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።