በምድርም ለተዘራው ዘርህ ዝናም ይዘንማል፤ ከምድርም ፍሬ የሚወጣ እንጀራ ወፍራምና ብዙ ይሆናል። በዚያም ቀን ከብቶችህ በሰፊና በለመለመ መስክ ይሰማራሉ፤
ኢሳይያስ 65:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ይቀመጡባቸውማል፤ ወይኑን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ቤት ይሠራሉ፤ በውስጡም ይኖራሉ፤ ወይንን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤትም ይሠራሉ ይኖሩበታል፤ ወይንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ቤት ሠርተው ይኖሩበታል፤ ወይን ተክለው ፍሬውን ይበላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቶችንም ይሠራሉ ይቀመጡባቸውማል፥ ወይኑንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ። |
በምድርም ለተዘራው ዘርህ ዝናም ይዘንማል፤ ከምድርም ፍሬ የሚወጣ እንጀራ ወፍራምና ብዙ ይሆናል። በዚያም ቀን ከብቶችህ በሰፊና በለመለመ መስክ ይሰማራሉ፤
“ይህም ምልክት ይሆንሃል፤ በዚህ ዓመት የዘራኸውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላቸሁ፤ ታጭዱማላችሁ፤ ወይንንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።
እኔም እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሀትን፥ ክሳትንም፥ ዐይናችሁንም የሚያፈዝዝ፥ ሰውነታችሁንም የሚያጠፋ ትኩሳት አወርድባችኋለሁ፤ ዘራችሁንም በከንቱ ትዘራላችሁ፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።
የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፤ የፈረሱትንም ከተሞች ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፤ የወይን ጠጃቸውንም ይጠጣሉ፤ ተክልን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።