ኢሳይያስ 46:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ዐስቡና አልቅሱ፤ የተሳሳታችሁ ሆይ፥ ንስሓ ግቡ፤ ልባችሁንም መልሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ በደለኞች፣ ይህን አስታውሱ፤ አስቡበትም፤ በልባችሁም ያዙት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን አስቡና አልቅሱ፤ ተላላፊዎች ሆይ፥ ንስሐ ግቡ፥ ልባችሁንም መልሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ ዐመፀኞች! በአእምሮአችሁ ያዙት፤ በልባችሁም አኑሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን አስቡና አልቅሱ፥ ተላላፊዎች ሆይ፥ ንስሐ ግቡ፥ ልባችሁንም መልሱ። |
አንቺም፥ “እኔ ለዘለዓለም እመቤት እሆናለሁ” ብለሻል፤ ይህንም በልብሽ አላሰብሽም፤ ፍጻሜውንም አላስታወስሽም።
አላወቅህም፤ አላስተዋልህም፤ ጆሮህን ከጥንት አልከፈትሁልህም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ፥ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ ዐውቄአለሁና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ በአእምሮ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃናት ሁኑ፤ በዕውቀትም ፍጹማን ሁኑ።