ኢሳይያስ 46:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 በጫንቃቸው ላይ ተሸክመውት ይሄዳሉ፤ በስፍራውም በአኖሩት ጊዜ በዚያ ይቆማል፤ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይሰማውም፤ ከክፉም አያድነውም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 አንሥተው በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ እቦታው ያደርጉታል፤ በዚያም ይቆማል፤ ከዚያም ቦታ አይንቀሳቀስም፤ ማንም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይመልስም፤ ከጭንቀቱም አያድነውም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል፤ በስፍራውም ያደርጉታል፥ በዚያም ይቆማል፤ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 አንሥተውም በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ በአንድ ቦታም ሲያኖሩት በዚያው ይቆማል፤ ካለበት ስፍራም መንቀሳቀስ አይችልም። ማንም ሰው ወደ እርሱ ቢጸልይ መልስ አይሰጠውም፤ ወይም ማንንም ከጥፋት ሊያድን አይችልም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል በስፍራውም ያደርጉታል፥ በዚያም ይቆማል፥ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፥ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም። Ver Capítulo |